የካሊስን ወደብ ጥሰው ለመግባት የሞከሩ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የፈረንሳይ ባለስልጣናት ማርች 3 ላይ እንደገለፁት ወደ 63 የሚጠጉ ስደተኞች የካሊስን ወደብ ሰብረው ለመግባት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ከእነዚህ ስደተኞች አብዛኛዎቹ አፍጋኒስታውያን፣ ፓኪስታናውያን፣ ኤርትራውያን እና ሶማላውያን ናቸው።
መጀመርያ ማርች 2 ማታ ላይ ወደ 100 የሚጠጉ ስደተኞች ወደ እንግሊዝ ለመሄድ በማሰብ የወደቡ አጥር ለመዝለል ሞክረው ነበር።
ከፍተኛ የሪጅኑ ኦፊሰር ጂን ፍሊፕ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለፀው ከዶቨር የመጡ ወደ 50 የሚሆኑ ስደተኞች ቦታቸው እንድይዙ መደረጋቸው ገልፀዋል። አነስተኛ ጀልባው 211 ስደተኞች እና 75 የጀልባዋ ቡድን ይዞ እንደመጣ ነው የተነገረው።
ወደ ጀልባዋ ጫፍ በመውጣት እየተንቀጠቀጡ በእግራቸው ሲሄዱ በፖሊስ እንዲወርዱ መደረጋቸውም ታውቀዋል።
“በዚህ መንገድ ሲሄዱ ከነበሩ ስደተኞች ሁለቱ ወደ ባህሩ የወደቁ ሲሆን በህይወት አድን ሰራተኞች ተርፈዋል።” ብለዋል ቬኒን። የወደቁት ስደተኞች “ሃይፎተርሚክ” ከመሆናቸው ውጪ ያጋጠማቸው ነገር የለም።
ጂን ማርክ ለጋዜጠኞች “ስደተኞቹ የፔዲስትርያን መንገድ ጥሰው የሄዱ ሲሆን እንደ’ኔ እምነት ከሆነ ይህ የተፈጠረው ህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች ያቀነባበሩት ሴራ ነው።” ብለዋል።
ስደተኞች ከብሪግዚት በፊት የእንግሊዝ መሬት ለመርገጥ እየፈሩ መምጣታቸው የምያወሱ ወሬዎች ይሰማሉ። ይህ ፍርሃት ደግሞ ህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎቹ እና ስደተኞቹ ሌላ ዓይነት ስልት ወደ መቀየስ ሊሄዱ ይችላሉ የሚል የባለስልጣናት መላ ምት አለ።
ከብሪግዚት በኋላ እንግሊዝ በአሳይለም ጥያቄ እና አጠቃላይ በስደት ዙርያ ያሻሸለችው ሆነ ያወጣችው አዲስ ፖሊሲ እስካሁን ይፋ የሆነ ነገር የለም። ይህ ማለት አሁንም እንግሊዝ ሀገር የገባ ስደተኛ ወደ ፈረንሳይ የመመለሱ ስራ አሁንም ከቦታው ነው። እንዲሁም በዱብሊን ረጉሌሽን መሰረት አንድ ስደተኛ አሳይለም መጠየቅ ያለበት መጀመርያ በረገጠው የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር መሆኑ ቀጥለዋል። ጃንዋሪ 2019 ላይ እንግሊዝ የሚመጡባትን ስደተኞች ወደ ፈረንሳይ መመለስ .ጀምራለች።
“100 ስደተኞች ሃቡርን ወደ መሰለ ቦታ ሰብረው መግባት መቻል ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ መሆናቸው ያሳያል” ብለዋል ካሊስ።
ትራፊክ በመዘግየቱ ምክንያት ቢያንስ ሁለት ጀልባዎች ባህሩ ላይ እንዲቆዩ ሆነዋል።
ይህ ሁነት የተፈጠረው የፈረንሳይ ፍርድቤት ለሶስት ህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች በእስር በቀጣበት ከአንድ ቀን በኋላ ነው። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የቡዱኑ ሊቀመንበር እንደሆነ የተነገረው ኢራቃዊ የ32 ዓመቱ ወጣት ሲሆን የ18 ወራት ፍርዱ የተሰጠው በቡሎግኒ የተባለችው የፈረንሳይ ሰሜናዊ ክፍል መሆኑ ታውቀዋል። ሁለቱም ጓደኞቹ ደግሞ አንዱ የ30 አመቱ ኢራናዊ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የ39 አመቱ ኢራቃዊ ነው። ሁለቱም ለአንድ አመት እንዲታሰሩ ተፈርዶባቸዋል። ሌሎች ሶስት ደግሞ ከፈረንሳይ እንዲወጡ ተደርጓል።
TMP – 07/03/2019
ፎቶ: ኤን ስቲወርት/ሻተርስቶክ
የ DFDS የባህር መንገድ ጀልባ በካልያስ ፖርት
ፅሑፉን ያካፍሉ