ሊብያ ውስጥ ስደተኞች ለትርፍ ሲባል ታግቷል ከባህር ውስጥ ይልቅ በየብስ ጉዞ ህይወታቸው የሚያልፉ ስደተኞች ይበዛሉ። በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር የተዘጋ ቢሆንም ኤርትራውያን አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸውን አላቋረጡም ጣልያን ፤- በባህር ላይ ተገኝተው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በሚገደዱ ስደተኞች ላይ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አድሳለች ኢትዮጵያ ፤ ለስደተኞችና ለዜጋዋ እኩል እድል የተረጋገጠባት አገር

50% በስደተኞች ላይ የሚደርሰው የመብት ጥሰት ሃላፊነቱ የሚወስዱት ህገ ወጥ ደላሎች ናቸው

50% በስደተኞች ላይ የሚደርሰው የተለያየ ጥቃት በተለይም ደግሞ ወሲባዊ ጥቃት፣ አካላዊ ጉዳት፣ ስርቆት እና ጠለፋ በህገ ወጥ ደላሎች የሚፈፀም መሆኑ   ሚክሲድ ማይግሬሽን ሰንተር  (MMC) የተባለ ተቋም ገልፀዋል። የዚህ ጥናት መሰረት  የ10 ሺ ስደተኞች ቃለ መጠይቅ ነው። ተቋሙ በ2018 ሪፖርቱ እንደገለፀው ሰዎች እንዳይሰደዱ የምያድረጉ ፖሊሲዎች ስደትን ሊገቱት አልቻሉም።  

ህገ ወጥ ስደት መቀነስ ላይ ከመስራት ይልቅ ህገ ወጥ ደላሎች የሰውን ህይወት የሚያባላሹበትን መንገድ እና ስልት ማጥናት እንዲሁም ስደተኞች የሚሄዱባቸው መንገዶች አደገኛነታቸው የሚቀነስበት ጉዳይ ላይ መስራት ያስፈልጋል።  በዚሁ ክፍለዘመን ቢያንስ 60 ሺ ስደተኞች በየመንገዱ ቀርተዋል።  በመሆም መንግስታት የስደትን መጠን መቀነስ ላይ የሚሰሩ ከሆነ አሁንም ህገ ወጥ ደላሎች ተጨማሪ ዕድል የምያገኙበት አጋጣሚ ነው እየሰፋ የሚሄደው።” ብለዋል የሚክስድ ማይግሬሽን ሴንተር መሪ የሆኑት ብራም ፍሬውስ።  

ህገ ወጥ ደላሎች የሚፈልጉዋትን የገነት ህይወት ለማግኝት ሲሉ የማያደርጉት ነገር የለም። ሰዎች ስደት እስካላቆሙ ድረስ ህገ ወጥ ደላሎች አሉ።” ሲሉም ጨምረው አብራርተዋል።  በዓለም አቀፍ ደረጃ በ 2016 ቢያንስ 2.5 ሚልዮን ህዝብ ለገንዘብ ሲባል በህገ ወጥ ደላሎች ተይዘዋል።  በዚህም ምክንያተ እስከ 7 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ዘርፈዋል።     በጥናቱ መሰረት በዚሁ የስደት ጉዞ ላይ አንድ ሶስተኛ ወይም ወይም ግማሽ የምያክል ስደተኛ ወሲባዊ አልያም አካላዊ ጥቃት  እንደደረሰበት ተነግረዋል። ተሰርዋል ተጠልፈዋል።  

ስደተኞች የሚሄዱበት መንገድ እንደየ ስደተኛው ፍላጎት እንደሚለያይ ሪፖርቱ አመልክተዋል። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ   በምዕራብ አፍሪካ የሚደረግ የስደት መንገድ በዋነኛነት ኢኮኖምያዊ መነሻ አለው። በአፍጋኒስታን በኩል የሚታይ የስደት መንገድ ደግሞ በዋነኛነት የመብት ጥሰት እና የፀጥታ ስጋት ነው መነሻው።  ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአፍሪካ ቀንድ ወደ ሳውዲ እና የመን የሚደረጉ የስደት ፍሰቶች መሰረታዊ የመብት ጥሰቶች ነው  መነሻቸው። ብዙ ስደተኞች በስደት መንገዳቸው አሰቃዊ መከራዎች ያጋጥማቸዋል። ይሁንና  ወደ 70% የሚሆኑት ያ ሁሉ ችግር እያወቁ አሁንም ወደ ስደት ድጋሚ ለመሄድ ይዘጋጃሉ። ይህ የምያሳየው የሰዉ የስደት ፍላጎት አሁንመ በጣም ከፍተኛ ነው።” ብለዋል የተቋሙ መሪ ፍረውስ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ራሳቸው በስህተት መንገድ በመሄድ እያሉም ቢሆን አብዛኞቹ ሌሎች እንዳይከተልዋቸው ይመክራሉ። ፍሬውስ እንዳሉት “60% የምያህሉ የቃለ መጠይቁ አካላት እንዳሉት ሌሎች ይሄንን ምርጫ እንዳይወስዱ ይመክራሉ።”

TMP – 27/11/2018

የሮያሊቲ ፍሪ ስቶክ ፎቶ መለያ ቁጥር  ID: 1185235300

የፎቶ ካፕሽን:  በርኮሰቭ ሰርብያ፤  ስደተኞች በኮራትያ ሰርብያ ዳርቻዎች ላይ ሻንጣዎች ተሸክመው ሲሄዱ