ኢራናውያን ቤተሰብ የእንግሊዝ የባህር ወሽመጥ ለማቋረጥ ያደረጉት ተደጋጋሚ ጥረት

አሕመድ ዓሊ ህጋዊ ያልሆነ ኢራናዊ ስደተኛ ሲሆን አይቲቪ ለተባለው የዜና ወኪል ባደረገው ንግግር ከሚስቱና ከሁለት ልጆቹ ጋር ወደ እንግሊዝ አገር ለመሰደድ ወይ ለመሻገር በካሌስ ፈረንሳይ እንደሚኖር ገልፀዋል።

በመጀመርያ ሙከራቸው ማለት መጀመርያ ባደረጉት የስደት ሙኮራ በባህር ዳርቻ በፈረንሳይ ፖሊሶች እንዲቆሙ ተደርጓ። በሁለተኛ ሙከራቸውም ተሳፍረውባት የነበረችውን ጀልባ ወድያውኑ በመስጠም በመጀመርያዋ እየዋኙ ወደ ፈረንሳይ አገር እንዲመለሱ ተገደዋል።

በሰዎስተኛው ሙከራቸውም በአሳ ማጥመጃ ጃልባ 10 ኪሎሜትሮችን ያህል እንደተጓዙ ጉዘኣቸው በፈረንሳይ ፖሊሶች ተጨናግፈዋል።

አሁንአሕመድ በጃልባ ወደ እንግሊዝ አገር ለመሻገር ወይ ለመሰደድ እንደማይሞክር ይናገራል። ምክንያቱም ጉዞው ለሴት ልጁ በጣም አደገኛና አስቸጋሪ በመሆኑ ነው። ሴት ልጁ በደረሰባት ጭንቀት ምክንያት በስነልቦናዊ ባለሞያ እየተረዳች ትገኛለች።

“ አሁን ልጄ በትክክለኛ ሁኔታ አትገኝም። በመጥፎ ሁኔታ ትገኛለች። ጥሩ ስሜትም አይሰማትም። ሃኪም ልጃችን በጥሩ ስሜት ላይ እንዳልሆነችና የዚህም ምክንያት ብቸኛ በመሆንዋ፣ ጓደኞች ስለሌሏት፣ ውደ ትምህርት ቤት ስለማትሄድ፣ ከእኩያዎችዋ ጋር ስለማትጫወትና በቋንቋዋ ባለመናገርዋ ሲሆን ከዚህ ለመላቀቅም ተገቢውን እንክብካቤ እንድናደርግላት ሓኪሙ ገልፀልናል። “ ሲል ተናግረዋል

ምንም እንኳን ሓኪሞች ለቤተሰቡ ለግዜው በልዩ ግዝያዊ ማረፍያ እንዲቆዩ ትእዛዝ የሰጡ ቢሆንም፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ ይደረጋል።

“ ቤተሰቤ እንደገና ወደ ጫካ ለመመለስና ለመደበቅ በጣም ፈርተዏል፤ ቤት የለንም፣ ሌላ አማራጭም የለንም፤ ስለዚህ ለመመለስ ተገደና” በማለት ሁኔታውን ለፕረስ አሶሴሽን ተናግረዋል።  አሕመድ በፈረንሳይ የጥገኝነት ጥያቄ ለማቅረብ አይችልም። ምክንያቱም በደብሊን ሕግ ወይ መተዳደርያ ደንብ መሰረት ወደ ዴንማርክ እንዲመለስ ይገደዳል። ይህም የሚሆንበት ምክንያት በዴንማርክ ሀይማኖቱን ወደ ክርስትና በመለወጥ ምክንያት ያቀረበው የስደተኝነት ጥያቄ ውድቅ በመደረጉ ነው።

ክሌር ሞስሌይ የተባለች የቻሪቲ  ኬር ፎር ካሌስ ግበረሰናይ ድርጅት ሰራተኛ “ይህ ሁኔታ በአውሮፓ ውስጥ እንግዳ ነገር እንዳልሆነና ብዙ ሰዎች በአውሮፓ ውስጥ ሲንከራተቱና የጥገኝነት ጭያቄ በተሳካ መንገድ ለማቅረብ እንደማይችሉ ለዚህ ዋናው ምክንያት የደብሊን ሕግ መሆኑን “ ትናገራለች

TMP – 25/02/2019

ፎቶ  ህገ-ወጥ የስደተኞች መጠልያ ካሌ

ስለ ስደት ማወቅ የምትፈልጉት ማነኛውም አይነት ጥያቄ በኢመይል አድራሻችን ልታገኙን ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቻችሁ በኢመይል አድራሻችን ላኩልን። ባልደረቦቻችን በፍጥነት ይመልሱላቹኋል። ሁሉም የኢመይል መልእክት
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው።

ስደት አስበዋል? ለምክር አገልግሎት ይደውሉልን


ፈረንሳይ ውስጥ ከሆኑ

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ