በፈረንሳይ የምትገኝ ትንሽ ከተማ አሳይለም ጠያቂዎችን ወደ ስራ እንዲሰማሩ በማድረግ ላይ ነች።
ፈረቴ በመባል የምትጠራው ከ800 የማይበልጥ ህዝብ የሚኖሩባት በምስራቃዊ የፈረንሳይ ክፍል የምትገኝ ከተማ ነች። ይህች ከተማ አሳይለም ጠያቂዎችን አርሂቡ ብላ በመቀበል ስትሆን እስካሁን የገባ ስደተኛ የህዝቧ 10% ሆነዋል።
ይህች ስዊዘርላንድን በሚያዋስን አምባ ላይ የተቆረቆረች ከተማ ከ2016 ጀምሮ ህፃናትን ጨምሮ ወደ 80 የሚጠጉ ስደተኞች ተቀብላ እያኖረች ትገኛለች። እነዚህ ከአፍጋኒስታን፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ቺቺንያ እና ናይጄርያ የመጡ ስደተኞች የያዘች ከተማ እንደ አሳይለም ጠያቂዎች ተቀባይነት እንድያገኙ ካልሆነም “የጥበቃ ድጋፍ” እንድያገኙ ጥያቄ ሲያቀርቡ የቆዩ ናቸው። የጥበቃ ድጋፍ ወይም ደግሞ ‘ሰብሲዳሪ ፕሮቴክሽን’ የሚባል ጥያቄአቸው ላልተመለሰላቸው ነገር ግን ድጋፍ እንደምያስፈልጋቸው ለታመነባቸው አካላት የሚሰጥ ድጋፍ ነው።
የከተማው ከንቲባ ፍራንኮይስ ኮሀደንት እንዳለው “በመጀመርያዎቹ አከባቢ ሀሳቡ የሚቃወሙ ሰዎች ነበሩ። በኋላ ግን የውስጣቸው ለውስጣቸው ያደረጉ ሰዎች እንዳሉ እንጃ እንጂ ብዙዎቹ ደስተኞች እየተቀበሉት መጥተዋል።” ብለዋል። በመጀመርያዎቹ አከባቢ ግን ስደተኞቹ “አንድም ስደተኛ ወደ ፍረቴ መግባት የለበትም።” የሚሉ እንዲሁም “ይህ ቤታችን ነው።” የሚል መልእክት ያላቸው መፈክሮች በመያዝ ሰለማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር።
አውሮፓ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ከፍተኛ የስደተኞች መጠን ማየት የቻለችው በ2015 ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጋ ስደተኛ ሲመጣባት ነው። ከዛ በፊት ስደተኞች ሌላ ቦታ ቢፈለግላቸውም የጠየቁትን የአሳይለም ጥያቄ ይዞት የሚመጣ ውጤት ብቻ እየጠበቁ ነበር የሚኖሩት።
ከንቲባው እንደገለፀው “የመጀመርያዎቹ ገቢዎች ሳንደል ጫማ የለበሱ ሁለት ጥቁር ሱዳናውያን ናቸው።” ብለዋል። በዚህ መልኩ የተጀመረ አሰራር ብዞዎቹ ሲደግፉት አንዳንዶች ደግሞ ተቃውሞአቸው ቤት እስከማቃጠል ደርሶ ነበር። ወደ ሆስፒታል የተወሰዱም ነበሩ።” ሲል አክለዋል። በፈቃድ የገቡ ስደተኞች የነሆይቦርስ አራውንድ ዘወርድ የተባለ ገባሪ ሰናይ ድርጅት ድጋፍም እንዳለው ተገልፀዋል።
“በእያንዳንዱ የማህበረሰባችን እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ እናደርጋለን። በበአላት፣ የአዲስ አመት አከባበር አብረውን እንዲዉሉ እናደርጋለን። ወጣ ስንልም ይዘናቸው በመሄድ ከማህበረሰቡ ጋር እንዲቀራረቡ እናደርጋለን።” ብለዋል የነሀይቦርስ አራውንድ ዘወርልድ ሀላፊ ኤልሳቤጥ ስቹልተስ።
አንድ ኮንጎአዊ ድጆ ካቡካ የተባለ ስደተኛ “አስላክ ዘረኝነት ያለበት አከባቢ ነው ሲሉ እሰማለሁ። ይሁን እንጂ አንድም ቀን ተሰምቶኝ አያውቅም።” ብለዋል።
የከተማይቱ ከንቲባ እንደገለፁት ከሆነ አሁን ያለው ችግር የህዝብ ትራንስፖርት ችግር ነው። ስደተኞቹ የምግብ አቅርቦት የምያኙት በ30 ኪሎሜትር ርቀት ከምትገኝ ማልሃውስ ከምትባል ከተማ ነው።
“በዚህ ከተማ በጣም ብርድ እንደገና ደግሞ በጣም ሙቀት የሆነ የአየር ሁኔታ አለ።” ብለዋል አንድ አልጀርያዊ ታዳጊ ስደተኛ።
እነዚህ አሳይለም ጠያቂዎች አሁን ያሉበት ቦታ ከአሁን በፊት የወተሃደር ካምፕ በነበረ እና አሁን ወደ ስደተኞች መቀበያ ማእከል በተቀየረ ቦታ ላይ ነው። ስደተኞች የአሳይለም ጥያቄአቸው ውጤት ከሰሙ በኋላ ወድያው ከማእከሉ ወጥተው እንዲሄዱ ይደረጋሉ።
የ’ሳብሲዳሪ ፕሮቴክሽን’ ዕድል ያላቸው ስደተኞች ደግሞ በካምፑ የመቆየት የሶስት ወር ዕድል አላቸው። ይህ የሚሆነው የራሳቸው የሆነ ስራ እንድያገኙ በሚል ነው። የአሳይለም ጥያቄአቸው ያልተመለሰላቸው ስደተኞች ደግሞ በቀጥታ ከፈረንሳይ እንዲወጡ ነው የሚደረገው። በ2018 ወደ ፈረቴ ከተማ ከመጡ 141 ስደተኞች 54% በከተማይቱ የመቆየት እና የ ‘ሰብሲደሪ ፕሮቴክሽን’ ዕድል አግኝተዋል።
TMP – 24/05/2019
Photo credit: ኦሲስቲ/ሻተርስቶስክ
ፈረቴ፤ በፈረንሳይ አሳንሲ ዞን የምትገኝ ትንሽ ከተማ
ፅሑፉን ያካፍሉ