በህገ ወጥ የሰው ዝውውር ወንጀል የተከሰሱ አካላት የፈረንሳይ ፍርድቤት የእስር ቅጣት ጣለ

ማርች 1 ቀን 2019 በዋለው ችሎት የፈረንሳይ ፍርድቤት በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተከሰሱ ሁለት ኢራቃውያንና አንድ ኢራናዊ ተከሳሾች የፍርድ ውሳኔ ጣለባቸው።  

የቡዱኑ መሪ እንደሆነ የታመነበት የ32 ዓመቱ ኢራቃዊ ሰው የ18 ወራት እስር የተፈረደበት በቡሉገር ሱር መር በተባለችው የሰሜናዊ ፈረንሳይ ጫፍ ከተማ በዋለው ችሎት ነው። ሁለቱ ግበረ አበሮች ደግሞ ማለትም  የ30 ዓመቱ ኢራናዊ እና የ39 አመቱ ኢራቃዊ ህገ ወጦች በአንድ አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስነዋል። ሶስቱም ህገ ወጥ የሰው ልጅ ዝውውር ተከሳሾች በፈረንሳይ ወሰን አከባቢ የተያዙ ናቸው።

ሰዎቹ ሊያዙ የቻሉት በዴሰምበር ወር መጀመርያ አከባቢ አንድ አብዛኛው ጊዜ ህገ ወጦች የሚጠቀሙባቸው  የጀልባዎች መሸጫ ያለው ነጋዴ በሰጠው መረጃ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል። ይህ ሰውዬ ተጠርጣሪዎች ሊገኙባቸው የምያስችሉ ሰነዶች እና ስልክ ቁጥር ሰጥተዋል።

ፖሊስ ጥብቅ ምርመራ ስያካሄድ ቆይቶ ጃንዋሪ 15 ቀን 2019 ሁለቱም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል። ሶስተኛው ሰው ሊያዝ የቻለው ስልኩ ሪከርድ ተደርጎ ሙሉ መረጃ ከተያዘ በኋላ መሆኑም ታውቀዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ሶስቱ የተለያየ ታሪክ የተናገሩ ሲሆን ከሶስቱ አንዱ ከህገ ወጥ የሰው ልጅ ዝውውር ጋር ንኪኪ እንዳለው ገልፀዋል። ሁለቱም ግን “ወደ እንግሊዝ ለመሄድ” አስበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸው ብቻ ተናግረዋል።   

ይሁንና ተጨማሪ ምርመራው እንደአረጋገጠው ሰዎቹ ህገ ወጥ ስደተኞች ለማዘዋወር የምያስችሉ ሰባት ጀልባዎች እያዘጋጁ የነበሩ ናቸው። ኦፕሬሽኑም በካሊስ በኩል አድገው ወደ ሳነጋቴ፣ ዊሳንትና አውደጊን ከዛ ወደ እንግሊዝ ለመድረስ የታሰበ መንገድ እንደነበር ለማወቅ ተችለዋል።  

ተጠርጣሪዎቹ በህገ ወጥ የሰው ልጅ ዝውውር የተገኙት አንዴ አይደለም። በተደራጀ የዝውውር ወንጀል ውስጥ የነበሩ ናቸው።” ብለዋል አቃቤ ህግ ካሚሊ ጎርሊን።

በኢራናዊው ተጠርጣሪ ስልክ ውስጥ በርከት ያሉ የጀልባ ፎቶዎችን ተገኝተዋል። የ39 አመቱ ኢራቃዊ ተጠርጣሪ የያዘው ስልክ ደግሞ ሁሉ ጊዜ የጀልባ አቅርቦት ወደላቸው አከባቢዎች አቅራብያ እንደነበር ተረጋግጠዋል።

የ32 አመቱ ኢራቃዊ ተጠርጣሪ የያዛት የስልክ  ቆፎ ይዞት የቆየው መልክእት “የእንግሊዝ መስመር ሲሻገሩ ያሉት ቦታዎች ስም ይገኙበታል።” ብለዋል አቃቤ ህጉ። አክሎም ተጠርጣሪው ወደ ቦታው ሳይጠጋ  የእንግሊዝ መሻገርያ መንገድ በጥብቅ ክትትል ውስጥ አስገብቶ ይቆጣጠረው እንደነበር ገልፀዋል። እናም ጠበቃዋ “የተደራጀ ቡድን መሪው እሱ ነው።” ብለዋል።

ከፈረንሳይ የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ወደ እንግሊዝ ለመሄድ በስደተኞች የሚደረግ ሙከራ ከመጀመርያዎቹ የ2018 ወራት ጀምሮ እስካሁን እየጨመረ መጥተዋል። የፈረንሳይ የጠረፍ ላይ ጠባቂዎች የያዙት ሪኮርድ እንደምያሳየው በ2018 አመቱ ሙሉ 78 ሙከራዎች የተደረጉ ሲሆን በ2019 በጃንዋሪ እና ፌቡራሪ ወራት ብቻ ግን 50 ሙከራዎች ተደርጓል።

ፈረንሳይና እንግሊዝ እየጨመረ ያለው ህገ ወጥ የስደተኞች ዝውውር ለመቆጣጠር በወደቦቻቸው ዙርያ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታና ድህንነት ስራዎች እየሰሩ ነው።

TMP – 22/03/2019

ፎቶ: ሃራልድ ስችምድት / ሻተርስቶክ. የእንግሊዝ የወደብ ፓትሮል ከነ የፀጥታው ቡድን