የእንግሊዝ የባህር ወሽመጥ ለማቋረጥ ከሚሞኩሩት ስድተኞች የተነገረ በጣም አሳዛኝ ታሪክ

በሰሜናዊ ፈረንሳይ የሚገኙት ስደተኞች የእንግሊዝ የባህር ወሽመጥ ለማቋረጥ በተደጋጋሚ ህይወታቻውን አደጋ ውስጥ ይጥላሉ።

ዓዚዝና መሪየም የተባሉት ባልና ሚስት ቢያንስ ለሃያ ግዜ ያህል ያደረጉትን  ሙከራ መክሸፉን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምንም እንኳን ወደ እንግሊዝ  / UK  / ቢገቡም በደብሊን ሕግ መሰረት ወደ ፈረንሳይ ተመልሰው ሊላኩ ይችላሉ።

ባለፈው አመት ጥቅምት ወር ላይ ቺያ ከተባለችው የአምስት አመት ልጃቸው ጋር በመሆን ወደ ዲንኪርክ ፈረንሳይ ተሻጋግረዋል።

የመጀመርያው እቅዳቸው በአየር በተሟላ ጃልባ የብርታንያ ዳርቻዎችን ለመድረስ ነበር ። ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ጉዞው ዋስትና ያለውና ብሪታንያ ቦታ እስከሚደርሱ ድረስም እንደሚሸንዋቸው አረጋግጣላቸው ነበር።

“ ሁሉም ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ወደ እንግሊዝ ቦታ ስትደርሱ ወደ ፖሊስ መደወል እንደአለባቹሁና ፖሊስም ወደ እንግሊዝ ለመግባት ያግዛቸዋል እንደሚሉዋቸው ዓዚዝ ተናግረዋል። ሆኖም ግን በጀልባ ጉዞ ካደረጉት ስድተኞች በሰሙት በጣም አሳዛኝ ምክንያት ያቀዱቱን የጃልባ ጉዞ ለመተው ወሰኑ።

አንድ ኢራናዊ ባለትዳር ከሁለት ልጆቹ ጋር ባደረገው የጃልባ ጉዞ ከአስራ አምስት ደቂቃ በሃላ  ጀልባው በመገልበጡ ምክንያት የመስጠም አደጋ አጋጥማቸው ነበር። “ ውሃው በጣም ቀዝቃዛ እጅግ ቀዝቃዛ ነበር። እግሮቼ ሙሉ በሙሉ ቀዝቅዘው ነበር። ይህም ሞትን እንድመኝ አድርጎኛል። በማለት ከልጆቹ አንዱ ተናግረዋል።

ሌሎች ሰለሞንና ሲሪ የተባሉት ባልና ሚስት የጀልባው ሞተር በመቆሙ /በመበላሸቱ ምክንያት ለሰዓታት በባህር ያለ ረዳት እንዲቆዩ ተገደዋል። ጀልባው በኮሮሲቭ በተባለ ነዳጅ ተሞልቶ ነበር። “ቆዳችን በመቃጠሉ ምክንያት በጣም የሚያም የሚያሳቃይ ነበር።“  በማለት ሰለሞን ሁኔታውን ይገልፃል።  ከሰዓታት በሃል ከአደጋው በመዳን ወደ ፈረንሳይ እንዲመለሱ ተደርጓል።

በጓደኞቻቸው በተነገራቸው አስፈሪ ታሪክ ምክንያት ዓዚዝ በጭነት መኪና ወደ እንግሊዝ ለመጓዝ ውሳኔ አደረገ። እናቱም ቤትዋ በ10000 የእንግሊዝ ፓውንድ ዋስትና በማስያዝ በኢራቅ ለሚገኙት ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎችና  ሽርካዎቻቸውን ትከፍል ነበር።

ለመሰደድ ባደረጉት ያልተሳኩ ሙከራዎች ምክንያት ብዙ ችግሮች አጋጥማቸዋል። አንዳንድ ግዜ የጭነት መኪኖቹ ወደ እንግሊዝ ከመሄድ ይልቅ ወደ ስፔንና ሩማንያ ይጓዙ ነበር። ሌላ ግዜም በአነፍናፊ ውሾች ተይዘዋል። አንዴም ለማቃዝቀዝ በሚያገለግለው የጭነት መኪና እንዲጓዙ ተደርጓል። ቅዝቃዜውም የማይቻል ነበር።

በመጨረሻ በጥቅምት 16 ቀን 2019 እ ኤ ኣ በሩማንያ የጭነት መኪና በመደበቅ በኢሮታነል ወደ እንግሊዝ// ገብተዋል።ሽፌሩ ከመኪናው እንዲወርዱ ካደረገ በኋላ በዘመደቻቸው በመታገዝ የጥገኝነት ማመልከቻ ለማቅረብ ወደ ፖሊስ ጣብያ እንዲሄዱ ተደርጓል። ሆኖም ግን በደብሊን ሕግ መሰረት ወደ ፈረንሳይ ሊመለሱ ይችላሉ።

TMP – 28/02/2019

ፍቶ- ጂኤል ኤፍ ሚድያ / ሻተርስቶክ/

የኣየር ላይ ፎቶ ዶቮር ወደብ ከእንግሊዝ የባህር ስላጤ የመጣ የመመላለሻ ጃልባ፡- ይህ የባህር ስላጤ በዓለም ውስጥ ከሚገኙ የውሃ ማመላለሻዎች በጣም ስራ የሚበዛበት የተጨናነቀ ሲሆን ይህም ታላቋ ብርታንያ ከአውሮፓ መሬት በዋናኛው ወደ ፈረንሳይ ወደቦች እንደነ ካሌስና ዲንኪሪክ ያገናኛል።