ፈረንሳይ ጥብቅና ሰብኣዊነትን የተሞላበት የስደተኞችፖሊሲ ትከተላለች

የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር፡- ፈረንሳይ በሌሎች አገሮች ተቀባይነት ያጡትን የፖለቲካ ተገን ጠያቂዎች የይግባኝ ሰሚ አትሆንም ብለዋል።

አዲሱ የተሸሙት የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ክሪስትፍ ካስታነር እንደገለፁት ከሆነ ፈረንሳይ በሌሎች አገሮች ተቀባይነት ያጡትን ተገን ጠያቂዎች የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አትሆንም ሲሉ ተናግረዋል። ይህን የገለፁት በፈረንሳይኛ ለሚታተመው ሳምንታዊ ጋዜጣ ለዥክናል ዱ ዲማንሼ ጥቅምት 21/2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። ካስታነር ጨምረው እንደገለፁት በፈረንሳይ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት የተገን አመልካቾች በሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሃገራት ውድቅ የተደረገባቸው ናቸው።

’’ በጀርመንና ጣልያን የመሳሰሉት አገሮች የተገን ጥያቂዎች ውድቅ የሆኑትን እኛ የይግባኝ ፍርድ ቤት መሆን አንፈልግም በማለት ገልፀው ፤ ፈረንሳይ በጣም ሃይለኛና ጥብቅ የሆነ ነገር ግን ሰብአዊነት የተላበሰ የስደተኞች አቀባበል ፖሊሲ እንደሚከተሉ ገልፀዋል።’’

በጥቅምት 16/2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ሆነው የተሸሙት ካስታነር በወሰንና ድንበሮች አከባቢ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ይፈልጋሉ፤ በተለይም በስፔይን በኩል ያለው በአውሮፓ ህብረት አባላት ካሉት ሃገራት በጣም ብዙ ስደተኞች በመቀበሏ፤  የስደተኞች ድርጅት እንደዘገበው ከሆነ ወደ 54 ሺ ህገ-ወጥ ስደተኞች ወደ ስፔይን እንደደረሱና ይህም በተመሳሳይ ጊዜ ወደ ጣልያንና ግሪክ ከደረሱት ስደተኞች ቁጥር ድምር (ብዛት) የሚበልጥ መሆኑ ዘግቧል።

“የስደተኞች ፍልሰት ወደ ስፔይን በ155% ጨምሯል በዚህ ዓመት። በፈረንሳይና ስፔይን ጠረፍ አከባቢ ህገ-ወጥ ስደተኞች በመሆናቸው ተመልሰዋል። ይህም 60% ጨምሯል ሲሉ ካስታነር ገልፀው ፤ በዚህ ጉዳይ ቁርጥ አቋም ሳንይዝና ህገ-ወጥ ስደተኞችን ወደ ሃገራቸው ስንመልስ ይህ ስናደርግ ደግሞ ሰብኣዊነት በተላበሰ ሁኔታ በመሆኑን ሳንዘነጋ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ካስታነር ጨምረው ከጣልያን አቻቸው ማቴዎ ሳልቪኒ ጋር ተገናኝተው መነጋገር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ይህም  ፈረንሳይ ህገ-ወጥ ስደተኞችን በጣልያን ጠረፍ ባለችው ከተማ አራግፋለች ተብላ ከተከሰሰች በሃላ ነው። ቀኝ ዘመም የጣልያን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ሰልቪኒ በስእል የተደገፈ ፎቶ በቲዊተር ገፃቸው የፈረንሳይ ፖሊስ ሁለት ስደተኞችን በድንበር ከተማ ባለው ጫካ ሲጥል በማሳየታቸውና ይህም ለአከባቢው ባለስለጣናት ሳያሳውቁ የተደረገ መሆኑ ገልፀዋል። ሰልቪኒ ብዙ የፖሊስ አባላት ድንበሩን የሚጠብቅ ማሰማራታቸውም ጨምረው ገልፀዋል።

“ጣልያን የአውሮፓ ስደተኞች ካምፕ መሆን አትፈልግም ፤ ለዚህም አትፈራም ፤ ከብራስልስና ከበርሊንም ትእዛዝ አትቀበልም ሲሉ ተናግረዋል። ሮም ውስጥ ያለዉን የፈረንሳይ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር እየጠበቅኩ ነው ፤ ነገር ግን የጠረፍ አከባቢዎችን ዳግም ቁጥጥር ማድረግም እንቀጥልበታለን ፣ ራሳችን ቀና ያደረግን ሃገር ነን ፤ ይህን ያልገባቸው ካሉ እንዲረዱት እንፈልጋለን” ብለዋል።

የጣልያን ጥብቅ ቁጥጥር ስራ የስደተኞችን ቁጥር ቀንሷል። በዚህ ዓመት ብቻ ከ 22 ሺ በላይ ስደተኞች ወደ ጣልያን ተጉዘዋል። ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 111 ሺ ነበር።     

TMP – 31/01/2019