በሊብያ ከሞት የዳኑት ስደተኞች ከተሳፈሩባት ጀልባ በሃይል እንዲወጡ ተደረጉ

ከ70 በላይ ከአደጋ የተረፉት ስደተኞች ወደ ሚሰራታ ከተማ ከተወሰዱ በኃላ ከህዳር 10/2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ ከጀልበዋ አንወጣም (አንለቅም) ስላሉ በሃይል እንዲወጡ እንደተደረገና በሊቢያ ውስጥ ወደ ጉዞ ከመነሳታቸው በፊት ብዙ ስቃይና እስራት እንደደረሰባቸው ገልፀዋል::

እንደ ተ.መ.ድ (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት) ዘገባ ከሆነ ስደተኞቹ ከኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ፓኪስታን ፣ ባንግላድሽና ሶማልና መሆናቸው ታውቋል:: እንደ ዜና ምንጮች ዘገባ ከሆነ ስደተኞቹ በአሁን ሰዓት በሊቢያ የሰደተኞች ማጎርያ ማእከላት እንዳሉና በዚህም የማይመችና ለብዙ ችግር የሚያጋልጥ ቦታ መሆኑ ይታወቃል::

አንዳንድ ስደተኞች ወደ ሊቢያ ከመመለስ ሞት እንደሚመርጡ ተናግረዋል:: አንድ የሱዳን ስደተኛ ለሮይተርስ እንደገለፀው ወደ ማንኛውም አገር ለመሄድ እንደሚሰማማና ወደ ሊቢያ ግን እንደማይሄድ ገልፃል::  ሌላው ስደተኛ ደግሞ እዛው ሊቢያ ውስጥ ለብዙ ጊዜያት እንደታሰረና ወንድሙም እዛው አንደሞተ ለአስሼትድ ፕሬስ በሰጠው ቃለመጠይቅ ገልፀዋል:: ወደ ሊቢያ መሄድ አንፈልግም ፤ ብትፈልጉ ሬሳችንን መውሰድ ትችላላቹሁ ብሏል::

የፓናማ ሰንደቅ አላማ የምታውለበልብ አንዲት ጀልባ (መርከብ) ኒቪን የተባለች 93 ስደተኞችን እንዳሳፈረች (እንዳጫነች) እና 28 ሌሎች የተረፋትንና በሌሎች 6 ጀልባዎች ሳይጫኑ የቀሩት ናቸው:: በፕላስቲክ ጀልባ ውስጥ ሆነን የድረሱልን ጥሪ ብናሰማም በዛች ለሊት ስድስት መርከቦች (ጀልባዎች) አልፈውን ሄደዋል፡፡  ማንም ሊያድነን የፈለገ የለም ፡፡(አልነበረም):: ዝም ብለው አልፈውን ሄደዋል፡፡ ሲል አንድ የሱዳን ስደተኛ ለሚድል ኢስት አይን ለተባለው ብሰጠው ቃለ መጠይቅ ገልፃል::

መርከቧ ብጥብቅ ቁጥጥር ላይ የነበረች ስትሆን የሊቢያ ቀይ ጨረታ ማህበርና አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ግን ለስደተኞች የምግብና መድሃኒት አቅርቦት ለማድረግ ፈቃድ አግኝተዋል:: ነገር ግን በካምፑ (ማእከሉ) ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት እንዳለና በተለይም የመፀዳጃና የንፅህና ጉድለት እንዳለበት ነው::

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደገለፀው ከሆነ የመርከቦቹ ወደ ሊቢያ መመለስ የአለም አቀፍ ህግን በግልፅ መጣስ መሆኑና ሊቢያም ለስደተኞቹ ምቹ ስፍራ አለመሆንዋ ያሳያል ብሏል::

በሊቢያ ስደተኞች አዘውትረው እንደሚታሰሩና ኢሰብአዊ የሆነ አያያዝ እንደሚገጥማቸውና የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች የስደተኞች እዛ መርከብ ውስጥ መመሸግ የሊቢያን ሁኔታ ያሳያል ብለዋል::   የመካከለኛው ምስራቅና የሰሜን አፍሪቃ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር የሆኑት ሂባ ምራየፍ ሲገልፁ የስደተኞች አመፅ (እምቢታ) በሊቢያ የማጎርያ ስፍራዎች ለስደተኞች የሚያጋጥማቸውን አስፈሪና አሰቃቂ ሁኔታ ያሳያል ብለዋል:: እነዚህም ሁኔታዎች   ግርፋት ስቃይና እንግልት እንዲሁም አስገድዶ መድፈርና ድብደባም ጭምርና ሌሎችም ስቃዮች ይደርሰባቸዋል::

የእርዳታ ድርጅቶች በዚህ ዓመት በሜዲትራንያን ባህር የሟቾች ቁጥር ሁለትሺ (2000) የደረሰ ሲሆን ከዚህም ግማሹ ከሊቢያ ወደ ጣልያን በሚደረገው ጉዞ መሆኑና በዚህም ምክንያት ጣልያን ከነሓሴ 2018 / ጀምሮ ወደቦችዋ ለነፍስ አድን ጀልባዎች (መርከቦች) ለመዝጋት ወስናለች::

TMP – 30/11/2018

ፎቶ ስደተኞችን በኒቨን መርከብ (ጀልባ) ውስጥ ሆነው በሚሰራታ ወደብ ሊቢያ