የጣልያን እምቢተኝነት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት የባህር ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ድጋፍ እያደረጉ ነው

2015 ጀምሮ በሜዲትራንያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ የሚደረግ ጉዞ ትልቅ በሚባል መጠን ከመቀነሱ ጋር ተያይዞ  የአውሮፓ ህብረት በኦፕሬሽን ሶፍያ የሚደረገውን የመርከብ እንቅስቃሴ እንዲገታ አዘዋል። የአየር እና የባህር ሀይልም 2015 ላይ በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት ህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር እንዲሁም በባህር ላይ አደጋ የሚደርስባቸው ስደተኞችን ለማዳን ሜዲትራንያን ላይ ከትመዋል። 

አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (አይኦኤም) ለጣልያኑ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ጠቅሶ እንደዘገበው በዚህ የፈረንጆች አመት እስከ አፕሪል 3 ቀን 2019 ባለው ግዜ ውስጥ ብቻ በባህር ወደ ጣልለያን የገቡት ስደተኞች ቁጥር 532 ነው። ማልታ ደግሞ 244 ስድተኞችን ለመቀበል ችላለች። የሊብያ የባህር ላይ ጥበቃ በበኩሉ 1,073 ስደተኞችን 2019 የመጀመርያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ ከመንገድ መልሶዋቸዋል።  

ወደ ጣልያን የገበቱት ስደተኞች በዚህ የፈረንጆች አመት ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲወዳደር  92%  ቀንሰዋል ተብለዋል። ይሁን እንጂ በባህር ላይ ያጋጠመ የሞት ብዛት ሲታይ ግን ላለፉት ሁለት አመታት ከተመዘገበው ቁጥር ብልጫ አሳይተዋል። በአሁን ሰዓት 10 ሰዎች አንዱ ይሞታል።  ከላፉት ሁለት አመታት ጋር ሲወዳደር ደግሞ ጭማሬ አሳይተዋል።

የአውሮፓ ህብረት የኦፕሬሽን ሶፍያን ሀላፊነት ሌሎችም እንዲወጡት የምያስችል መነሻ ሀሳብ ከማርች 31 ቀን 2019 ስድስት ወር አስቀድሞ አውጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ ጣልያን  ሌሎች የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የማይጋሩት   ከሆነ ስደተኞችን የመቀበል ጉዳይ በፍፁም እንደማታስበው ግልፅ አድርጋለች። በመሆኑም በዚህ መነሻ ሀሳብ የተስማማ አንድም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር በሌለበት ሁኔታ በባህር ስራዎች ላይ የተሰማራ ኦፕሬሽን ሶፍያ ስራ እንድያቆም ይገደዳል ማለት ነው።  

የባህር ላይ ፓትሮል በቆሙበት ሁኔታ ኦፕሬሽኑ በአየር ፓትሮል እና ከሊብያ የባሀር ጠረፍ ጠባቂዎች ጋር በመሆን ለመስራት እንደሚሞከር ተገልፀዋል። 

ድጋፍ ሰጪ ተቋማትና የሰብአዊ መብት ተሞጓቾች ይህ ውሳኔ እየተቹት ነው።

የምግባረ ሰናይ ተቋማት ጀልባዎች ከሜዲትራንያን ባህር እንዲወጡ ተደርጎ ባለበት ሁኔታ፤  የደህንነት እና የአደጋ ጊዜ ድጋፍ ሰጪ አካላት ስራ እንዳይሰሩ ታግደው ባሉበት ሁኔታ፤ የአውሮፓ ህብረት አመራሮች በባህሩ አከባቢ የነበሩ ጀልባዎቻቸው እንዲወጡ ወስነው የህፃናት እና ሴቶች ህይወት አወላላ ሜዳ ላይ እንዲቀር እያደረጉ ነው።ብለዋል የአሚኒስቲ ኢንተርናሽናሉ ማቲው ቢሊስ።

ይህ የምያሳየው የአውሮፓ ህብረት ስደትን ለመከላከል ሲል የሰው ልጅ ህይወት እንድያልፍ እያደረገ ነው። ይህ ደግሞ እንደማስተማርያ እየወሰደው ነው።ያለው ደግሞ የዶክተርስ ዊዝ ኣውት ቦርደርስ አባል የሆነው ሃሲባ ሃድጅ ሳህሮይ ነው። አያይዞምይህ በእንዲህ እንዳለ በሌላ በኩል ደግሞ የአውሮፓ ሃገራት ለሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ድጋፍ እያደረጉ ነው። ሊብያውያኑ ጠባቂዎች ሀላፊነት የማይሰማቸው ከመሆናቸው በላይ ስድተኞቹ አሰቃዊ እና ሰብአውነት የጎዳለቸው የስደተኞች ማእከላት ውስን እንዲታጎሩ እየተደረገ ነው።

ጣልያን ከአሁን ቀደም በወደቦችዋ አከባቢ ሲሰሩ የነበሩ በሰብአዊ ድጋፍ ዙርያ የሚሰሩ ተቋማትን ዘግታ እንደነበር   ይታወቃል። ከኦፕሬሽን ሶፍያ ጋር በቅርበት በመስራት በሜዲትራንያን ባህር የምያጋጥም የነበረ አደጋ በመከላለከል ረገድ ደህና ስራ ስደተኞቹ በመያዝ እና  በመመለስ  በኩል ጥሩ ስራ ሲሰራ የነበረ የሊብያው የጥበቃ ሀይሉ ነው።

TMP – 13/04/2019

ፎቶ ክሬዲት: ፖይንት ብሬክ/ሻተርስቶክ የጣልያን የአየር ፓትሮል በሜዲትራንያን ሰማይ ላይ፤ ኦገስት 2016