የህገ ወጥ ስደት አደጋዎች

በህገ ወጥ የሰው ልጅ ንግድ የተሰማሩ አካላት በጀልባ፣ ባቡር፣ በመኪናና ሌሎች ተመሳሳይ  የመጓጓዣ መንገዶች አማካኝነት ወደ እንግልዝ ሀገር ለመውሰድ ሊያግባብዎት ይችላሉ። ይሁን እንጂ ይህ መንገድ በጣም አደገኛ መሆኑ መታወቅ አለበት። ያለው አደጋ እንደሚከተለው ጠቅለል ተደርጎ ለማቅረብ ተሞክረዋል።  

በእነዚህ አደጋዎች ምክንያት ስጋት ካደረብዎት አሁኑኑ በሆትላይናችን ላይ አግኝተውን አስፈላጊውን መረጃ እና ወዴት መሄድ እንዳለባችሁ የሚነግር መረጃን ይውሰዱ።

 

 

ህገ ወጥ የሰው ልጅ ንግድ አካላት አብዛኛው ጊዜ የእንግልዝን ቻናል ለማቋረጥ ለአደጋ ተጋላጭነት ያላቸው ጀልባዎች ይጠቀማሉ።  በእንግልዝ እና ፈረንሳይ መሀከል ያለው የውሃ አካል ስደተኞች በብዛት ከሚተላለፉባቸው መስመሮች ተጥቃሹ ነው። በዚህ መስመር፡ ስደተኞች ለማለፍ የሚሞክሩ በሌሊት አልያም በንጋት ነው። አንዳንድ ስደተኞችም እየዋኙ ለማለፍ ይሞክራሊ። ይሁን እንጂ ውሃው በጣም ቀዝቃዛ  ሀገራቱም ጥብቅ ቁጥጥር የምያደርጉ በመሆናቸው ይህ የማይታሰብ እና አደገኛ ነው።

በታህሳስ 2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ ኢንግሊዝና ፈረንሳይ በመተላለፍያ ካናል የተመለከተ ስራ ለማቋቋም ተስማምቷል። የህገወጥ አዘዋዋሪዎች መረብ ለመበጣጠስ የሚያስችል ህግ ስራ ላይ ለማዋል ነው። ከዛን ጊዜ ጀምሮ የኢንግሊዝ መንግስት በካናሉ መተላለፍያ ዙርያ በአየር ፣ በጀልባ ፣ እግሮኞች ጀምሮ የኢንግሊዝ መንግስት በካናሉ መተላለፍያ ዙርያ በአየር በጀልባቾ እግረኞች በመዝናኛዎችና በባህር ዳርቻዎች አከባቢ የመከታተሉን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥልበት አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈረንሳይ በኖርድና ፓደ ካሌ አንድ የተግባር እቅድ እንዳዘጋጀችና ይህም የክትትልና የደህንነት ስራዎች በቦለኛና በሱር ሜር ወደቦች (ባህር) እና ካሌ እርምጃዎች እንድትወስድ የሚያስችላትን ስራ ይጨምራል። በተጨማሪም በባህር ዳርቻ መናፈሻዎችና ሌሎች ቦታዎች ህገወጥ ደላሎችና ስደተኞች ጀልባዎችን የሚያሰማሩበት ነው። የአከባቢ ነዋሪዎችም በጣም ንቁ ሆነውና ማንኛውም የሚያጠራጥር ነገር ካዩ ወይም ካጋጠማቸው ለፖሊስ ደውለው እንዲያሳውቁ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

በመኪና የሚደረግ ጉዞም በየአከባቢው ባለው የፍተሻ ማእከላት የመያዝ እድልዎ ከፍተኛ በመሆኑአደገኛ አማራጭ ነው።  የእንግሊዝ ባለስልጣናት በመኪና ለሚመጣ ስደተኛ ማንነቱ አጣርቶ ለመያዝ የምያደርጉት ፍተሻ ከረር ያለ ነው። ፍተሻው በቴክኖሎጂም የተደገፈ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ በሰዓት እስከ 250 ተሽከርካሪ የመፈተሽ አቅም አለው። በህገ ወጥ የሰው ዝውውር የተሰማሩ አሽከርካሪዎችን በጥብቅ የሚቆጣጠር ስርዓትም አላቸው።  

በዚህ መንገድ የሚደረገውን ጉዞ አደገኛ የምያደርገው የመያዝ እና በባቡር የመመታት ድልዎት ሰፊ ስለሆነ ነው። ከተያዙ በቀጥታ ይታሰራሉ። በዚህ ዙርያ የሚደረግ ክትትል በጣም ጥብቅ ነው።  ከ400 በላይ ሰኩዩሪቲ ካሜራዎች አሉ። በጣም ከፍታ ያላቸው አጥሮችም አሉት። እንዲሁም እነዚህ መከላከያዎች የሚከታተሉ ስታፍ አባላት ብዙ ናቸው። በዚህ መስመር የሚደረግ ጉዞ አደገኛ የምያደርገው ሌላ ምክንያት ባቡሮች በሰዓት እስከ 100 ማይልስ የሚምዘገዘጉበት ስለሆነ የኤሌክትሪክ አደጋ የሚገጥማቸው እና የሚሞቱ አሉ።

እነዚህ አካላት ለስደተኞቹ ያልሆነ መረጃ በመስጠት ነው ስራዎቻቸው የሚሰሩት። ከስደተኞቹ ህይወት በላይ ግድ የሚሰጣቸው ገንዘባቸውን መሰብሰብ እንጂ የሰው ልጅ ህይወት አይደለም። የተጠቀሱትን አደገኛ እና አስጊ የስደት መስመሮች ድህንነታቸው የተጠበቀ አስመስሎ በመስበክ እናም የማይመጣጠን ገንዘብ በመቀበል ህገ ወጥ የሰው ንግድ ስራው ያጧጡፉታል።  በዚህ ዙርያ ስደተኞች በቂ መረጃ ካልያዙ ወደ እስር፣ ዕዳ እና የጉልበት ብዝበዛ  ችግሮች ይጋለጣሉ።

በብዙ ውጣ ውረድና ችግር ኢንግሊዝ አገር የደረሱም ለደላሎች ብድር ለመክፈል በባርነት እንዲኖሩ ይገደዳሉ። ይህም ለሴተኛ አዳሪነትና የቤት ስውጥ አገልጋይነትን ይጨምራል።

ሴቶች በዚህ መንገድ ለምያጋጥሙ የመደፈር እና መጠቀምያ የመሆን  ችግሮች ከወንዶች በላይ ተጋላጭነት አላቸው። ከእነዚህ አይነቶቹ ፈተናዎች ለማምለጥ ለብቻቸው ይሄዳሉ። ይሁንና ችግር እየሆነ የመጣው ሌላ ጉዳይ ሴት ስደተኞች ራሳቸውን እያገለሉ በሄዱ ቁጥር የተሻለ አማራጭ እና ተጭማሪ ዕድሎችን ማግኘት ከምያስችሉ የመረጃ መረቦች   እየራቁ ይሄዳሉ።

ለዚህ ችግር ደግሞ ሴቶች የበለጠ ለወሲባዊ ጥቃት ተጋላጭ ይሆናሉ። አንዳንኤም ለሴተኛ አዳሪነት ተገደው ይገባሉ። ከህገ ወጥ ጉዞአቸው ጎን ለጎን ለወሲባዊ ጥቃት መጋለጣቸውም ከፍተኛ ነው። ህገ ወጥ ሰደተኞች በመሆናቸው መብታቸው ለማስከበርም ወደ ፖሊስ አይሄዱም። ወደ ኢንግሊዝ አገር እንደ ምንም ቢገቡም አብዛኛው ጊዜ መጨረሻቸው ለህገ ወጥ ደላሎች እዳ መክፈያና ለብዝበዛ የተጋለጡ ይሆናሉ።

በተጠቀሱት አስጊ መንገዶች እንግልዝ ሀገር የመድረስ ዕድል እንኳን ቢገጥሞት ተይዘው በሀይል እንዲመለሱ የማድረግ ሌላ ፈተናም አለ።   የአውሮፓ ህብረት ባወጣው ዱብሊን ረጉሌሽን ተብሎ በሚታወቅ ህግ መሰረት አንድ ስደተኛ አሳይለም መጠየቅ ያለበት በገባበት የመጀመርያ አውሮፓዊ ሀገር ነው። ይህ ማለት አሳይለም የመመለስ ሃላፊነት ያላቸው ስደተኛ እግሩ ያረፈበት የመጀመርያው ሀገር ላይ ነው ማለት ነው።  ስለሆነም አሳይለም ሊጠይቁ ወደ የሚገባዎትን ከእንግሊዝ ሌላ ወደ ሆነ ሀገር እንዲመለሱ ይደረጋል።

አሳይለም ለመጠየቅ የምያስችል በቂ ምክንያት የሌለው ስደተኛ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ነው የሚደረገው። አሳይለም መጠየቅ እንደማይችሉ ከተነገረዎት እና በፈቃድ መመለስ ካልቻሉ የእንግልዝ መንግስ ኢሚግሬሽን ኢንፎርስመንት (UK-IE) ተብሎ በሚታወቀው የሀገሪቱ ህግ መሰረት በሀይል እንዲመለሱ ይደረጋል።

ጥገኝነት (ተገን) ጠያቂዎች ጥያቄአቸው ውድቅ የሆነባቸውና በፈቃደኝነት የማይመለሱ ወይም ተገደው የሚመለሱ በኢንግሊዝ በህገ ወጥነት እየኖሩ ነው። ለእርዳታ ድጋፍ፣ ለጤና እንክብካቤና ሌሎችም ጥቅማ ጥቅሞች ብቁ አይደሉም ፤ በህገ ወጥነትም እየሰሩ ነው። ይህ ደግሞ ለብዝበዛ የተጋለጡ ያደረጋቸዋል ፤ የቀጣዩ ህጋዊ ጉዞ ማመልከቻቸውም ስኬት ያደናቅፋባቸዋል። .

እንደ አውሮፓ ህብረት ህግ ከሆነ አንድ ስደተኛ ከተያዘ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ከመደረጉ በፊት እስከ 18 ወራት ሊታሰር ይችላል።  በ2017 ብቻ በፈረንሳይ እስከ 47,000 የሚደርሱ ስደተኞች ታስረው ነበር። በፈረንሳይ ሀገር ያሉ እስርቤቶች የታፈኑ እና የማይመቹ ናቸው። ወደ ውጭ ለመውጣት ያለ እድል በጣም ጠባብ ነው፤ ወጥቶ ተዝናንቶ ለመግባትም ያለ ዕድል እምብዛም አይደለም።

እንግልዝም  በተመሳሳይ ስደተኞችን የምትይዘበት ማእከል አላት። በአውሮፓ ታላቁ እስር ቤት ያላት እንግሊዝ በ2018 ብቻ 29,000 ስደተኞች በተመሳሳይ ኬዝ ታስረወበት የነበረ ነው። ከእነዚህ እስረኞች 13,000 ያምያህሉ አሳይለም ጠያቂዎች ሲሆኑ 42 ደግሞ ተጋላጭነት ያላቸው (minors ) ናቸው። ከእነዚህ ስደተኞች አብዛኛዎቹ ወደየሀገራቸው ሌሎችደግሞ መጀመርያ ወደ ገቡበት ሀገር እንደሚመለሱ ይደረጋል። ለአጭር ጊዜ በሚቆይ እስርቤት የሚነሱ በርከት ያሉ ጥያቄዎች አሉ። የመብራት መቆራረጥ፣ የመኝታ እና የሻወር አቅርቦት በቂ አለመሆን ከብዝዎቹ የተወሰኑትን መጥቀስ ይቻላል።

ለሌላ ያካፍሉ

የእንገሊዝ ቻናል በማቋረጥ ላይ ለነበሩ ስደተኞች ድጋፍ አድርጋቹኋል የተባሉ ሁለት ፈረንሳውያን ታሰሩ

ሁለት ፈረንሳውያን ስደተኞች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው ወደ እንግሊዘ እንዲገቡ በማገዛቸው ምክንያት በእስር እንዲቀጡ...
ተጨማሪ ያንብቡ

በፓሪስ አየር መንገድ ተርሚናል በሀይል ወደ ሀገር ቤት አንመልስም ያሉ በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሰለማዊ ሰልፍ አደረጉ

በመተዎች የሚቆጠሩ ህገ ወጥ ስደተኞች በፈረንሳይ መዲናዋ ፓሪስ ከተማ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ በመሰባሰብ...
ተጨማሪ ያንብቡ

የፈረንሳይ የባህር ላይ ጥበቃ ሀይሎች የእንግሊዝ ቻናል አልፈው ለመሄድ የሞከሩ ዘጠኝ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

መይ እሁድ 19 ቀን 2019 ዘጠኝ ስደተኞች በመያዝ በእንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ እንግሊዝ በመሄድ ላይ የነበረ ትንሽ ጀልባ...
ተጨማሪ ያንብቡ