ገነዘብ ነክመ አደጋዎች
ያለ ህጋዊ ቪዛ ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ለመድረስ ስንት ወጪ/ዋጋ እንደሚያስከፍል መገመት ትችላላሁን? ወደ አውሮፓ ለመድረስ የሚደረገው ህገወጥ ጉዞ ዋጋው ውሰን/መደበኛ አይደለም። የክፍያው ሁኔታ በአያሌ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ሲሆን ይህም በሚጓዝበት መንገድ ፤ የህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ሁኔታና የመጓጓዣው ዓይነት ላይ የተመሰረተ ነው።
አብዛኛውን ጊዜ ስደተኞች በአእምሮአቸው በሚገምቱት ዋጋ ላይ ጉዞውን ይጀምራሉ። ይሁን እንጂ በጉዞው ላይ የሚከፍሉትን ዋጋ/ወጪ ይጨምራል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ለምሳሌ አጋቶች የማስለቀቅያ ገንዘብ ሊጠይቁ ይችላሉ ወይም ስደተኞች ሊታመሙ ስለሚችሉ ለህክምና እርዳታ ገንዘብ ሊከፍሉ ይችላሉ።
በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለሚሄድ ካሰባችሁ ስነ ገንዘብ ነክ ሁኔታዎችን/ወጪዎችን በሚመለከት በቂ ግንዛቤ ካገኛችሁ ወደ ፊት ለምትወስነት ውሳኔ በግንዛቤ ላይ የተመረኮዘ እንዲሆን ያስችላቹሃል።
ከስደተኞች ፕሮጀክት ጋር በተደረገው ቃለ መጠየቅ ከአፍሪካ ቀንድ ወደ አውሪፓ ለመድረስ 5400 የአሜሪካን ዶላር እንደሚከፍሉ ስደተኞቹ ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ለመድረስ 1600 የአሜሪካን ዶላር ገደማ የስከፍላል።
በተጨማሪም ከሱዳን ወደ ሊቢያ ለመደረስ 1600 የአሜሪካን ዶላር በስተመጨረሻም ሜዲትሪያንያን ለመደረስ እሰከ 2200 የአሜሪካን ዶላር ያስከፍላል። ምንም እንኳን ስደተኞቹ ይህን ያህል ብር ቢከፍሉም አውሮፓ ለመድረስ ዋስትና የላቸውም። ወደ አውሮፓ ለመድረስ ያቻሉትንም ቢሆን የመታሰርና ወደ አገራቸው የመመለስ ሁኔታዎች ሊያጋጥማቸው ይችላል።
አንደድ ስደተኛ ከስደተኞች ፕሮጀክት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በሜዲትሪያንያን በኩል ከሊቢያ ወደ አውሮፓ ለመድረስ 3 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስከፍል ተናግሯል። ሊቢያ ከደረሰም በኃላ ወደ አገሩ ለመመለስ ተገዷል። ምክንያቱም ባህሩን ለመሻገር ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች የጠየቁትን ገንዘብ ለመክፈል አልቻለም።
አብዛኛዎቹ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመጓዝ የሚከፍሉትን ገንዘብ/ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ግንዛቤ የላቸውም። ህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ወደ አውሮፓ ለመድረስ አስተማማኝ ርካሽ እንደሆነና በመሸጋጋሪያው ጊዜ በሚያርፍበት አገሮች ውስጥ የስራ ዕድል እንዳለ ስደተኞቹ ይነግራቸዋል። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። ህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች የስደተኞችን ለአደጋ ተጋላጭነትን በመመልከት ለምግብ ጥላ ማረፍያ ቦታ ወይም ባለስልጣኖችን ጉቦ ለመስጠት በሚል ሰበብ በተደጋጋሚ ብዙ ገንዘብ እንዲከፍሉ ያደርጓቸዋል።
ስደተኞቹ በየደረሱበት ቦታ እንዲከፍሉ የሚያደርግ ዘዴ/አሰራር እየተለመደ መጥቷል። ይህ አሰራር ስደተኞች ለአደጋና ተገቢ ባልሆነ መንገድ ገንዘባቸውን እንዲቀሙ ያደርጋል። ምንም እንኳን ወደ ፈለጉበት ቦታ ለመድረስ ዋስተና ባይኖራቸዉን እየከፈሉ ይገኛሉ። የሚከፍሉበት መንገድም ከቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ በመበደር ፣ ቤቶቻቸው ወይም የንግድ ድርጅቶቻቸውን በመሸጥ ነው።
ስደተኞች የአውሮፓ ምድር/ዳርቻዎች ከረገጡም በኃላ ወደ ፈለጉበት ቦታ እስከሚደርሱ ድረስ ጉዞአቸውን ይቀጥላሉ። በአውሮፓ መጓዝ በጣም ውድ ነው። ለምሳሌ አንድ ስደተኛ ከስደተኞች ፕሮጀክት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ከካሌስ ፈረንሳይ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለመድረስ 5 ሺ የአሜሪካን ዶላር ለህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች እንደከፈለ ተናግሯል።
በአውሮፓ የኑሮ ሁኔታ/ዋጋ እንደየአገሩ ቢለያይም ከስደተኞች አገር ጋር ሲነፃፀር ዋጋው በጣም ውድ ነው። በአውሮፓ አገሮች የሚገኙት ሀግ ወጥ ስደተኞች የስራ አጥነት ቁጥር የላቀው በዚህም ምክንያት የኑሮ ወጪያቸውን ሸፍነው ዕዳቸውን ለመክፈል ይቸገራሉ። ምንም እንኳን ህጋዊ ስደተኞች ከመንግስት የህክም፣ የትምህርትና የመኖርያ ቤት እገዛ የሚያገኙ ሲሆን ህገወጥ ስደተኞች ግን እነዚህን እርዳታዎች አያገኙም።
ከዚህ መረጃ በአውሮፓ ስላለው የስደተኛ ህይወት ምን እንደሚስል መገንዘብ ትችላላችሁ።
በህገወጥ ጉዞ ላይ ያልተጠበቀ ከፍተኛ ወጪ መክፈል ማለት ብዙ ስደተኞች ወደ ሳበቡት ቦታ ሳይደርሱ ወደ አገራቸው ይመለሳሉ ማለት ነው/እንዲመለሱ ይደረጋል። ከነሓሴ 2017 እ.ኤ.አ ጀምሮ አለም አቀፍ የሰደተኞች ድርጅት 102 ኢትዮጵያውያን ከሊቢያ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እርዳታ አድርጓል። ብዙ ስደተኞች በሊቢያ ያለ በቂ ገንዘብና እርዳታ በመኖር ወደ አገራቸው መመለስ ያዳግታቸዋል።
ከጥር 2017 እሰከ ግንቦት 2018 እ.ኤ.አ ባለው ጊዜ አለም አቀፍ የሰደተኞች ድርጅት በፈቃደኝነት የመመለስ ብሮግራም ከ23,300 ስደተኞች በላይ ከሊቢያ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።
ብዙ ገንዘብ የከፈሉ/ያጠፉ ስደተኞችም በፈቃዳቸው ወደ አገራቸው የመመለስ ፍላጎት አላቸው። ለምሳሌ በ2017 እ.ኤ.አ ከተለያዩ አገሮች የመጡ 30 ሺ የሚሆኑ ሰደተኞች በፍላጎታቸው ከጀርመን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ይህ የሚሆንበት ምክንያትም ስደተኞች ጉዞአቸው ከመጀመራቸው በፊት በአውሮፓ ያለዉን ህይወት ምን እንደሚመስል ባለመገንዘባቸው ነው።
ካልተሳካ ጉዞ በኃላ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ስደተኞች ብዙ መሰናክሎች ያጋጥማቸዋል። ብዙ ሰደተኞች ጊዜና ገንዘብ በማበከናቸው ምክንያት ፀፀት ይሰማቸዋል። ሌሎችም ከቤተሰቦቻቸውን ከአከባቢው ማህበረሰብ ቁጣ ይደርስባቸዋል። አንዳንድ ጊዜ በሰደት ብዙ ዓመታትን በውጭ አገር ያሳለፉ ስደተኞች የአገራቸው ህይወት እንደገና ለመልመድ ሲቸገሩ ይታያሉ።