አካላዊ ስጋት

ስደተኞች ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ለመድረስ አደገኛ በሆኑ ብዙ መንገዲች ይሞክራሉ ።

ይህም በከባድ መኪናዎችና ጀልባዎች በመሸሸግ ሲሆን ይህም ለአካላዊ ስጋት እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል። በደላሎችና ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ለስደተኞች ወደ አውሮፓ የሚደረገው ጉዞ ቀላልና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ይናገራሉ። ነገር ግን በደላሎች የሚደረገው ጉዞ ስደተኞቹን ለከፍተኛ አደጋ ፣ ስጋትና ብዝበዛ ያገልጣቸዋል።


ከአፍሪቃ ቀንድ አከባቢ ወደ አውሮፓ ለመድረስ በህገወጥ ስደተኞች ተመራጭ የሆነው የጉዞ  መስመር በሊቢያ በረሃዎች በኩል ሲሆን ከዛም የሜዲተራንያን ባህርን በማቋረጥ ጣልያን መግባት ነው። በየብስ የሚደረጉት ጉዞ አብዛኛዎቹ በመታፈን ወይም በጭስ ታፍነው ወይም በተበላሹ መኪኖች ጉዞው ከመጨ ረሻቸው በፊት ይጠላሉ።

ወደ አውሮፓ ለመድረስ የሚሞክሩ ስደተኞች አብዛኛው ጊዜ የሚጓጓዙት ከአቅም በላይ በተጫኑ ጀልባዎችና ለባህር ጉዞ ብቁ ያልሆኑና ደህንነታቸው ያልተጠበቀ አንዲሁም ተጓዥችን ለመሸከም የማይመጥኑ ጀልባዎች ናቸው። እንደ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ዘገባ ከሆነ እሰከ 2018 እ.ኤ. አ. ወደ 2300 የሚጠጉ ስደተኞች በሜዲተራንያን ባህር እንደሞቱና የአውሮፓ ባህር ዳርቻዎች ለመድረስ ሲሞክሩ ደብዛቸው የጠፉ እንዳሉ ታውቋል።

በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመድረስ በሚያደርጉት ጉዞ ስደተኞች በደላሎች አማካይነት ለአካል ጉዳትና የጉልበት ብዝበዛ እንዲጋለጡና ደላሎቹም ተጓዥችን መንገዱ ቀላል አጭርና ምቹ እንደሆነ ይዋሸዋቸዋል። በተጨማሪም አውሮፓ ሄደው የጥገኝንት ፈቃድ አንዲያገኙ በማጋነን  ይነግሩዋቸዋል።

ህገወጥ ደላሎች ሰዎችን ለሌላ ወረበሎችና ደላሎች እንደሚሸጡ ወይም ስደተኞችን በማገት የማስለቀቅያ ገንዘብ ይጠይቃሉ። ሰዎች ያለፍላጎታቸው  ተገደው እንዲሰሩና ምንም ዓይነት ደሞዝ ሳይከፈላቸው ያሰራሉ። ሰዎችን በማሰር በማሰቃየት አገር ቤት ካሉ ቤተሰቦች ገንዘብ በሃዋላ እንዲላክላቸው ያደርጋሉ ። አንድ ስደተኛ  ከቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ጋር ግንኙነት ካቋረጠ ስደተኛው ለብዝበዛና ስጋት ተጋላጭ እንደሚሆን ደላላው ያውቃል።

ህገ ወጥ ደላሎች ለያንዳንዱ የጉዞ ደረጃ ብዙ ገንዘብ ይጠይቋቸዋል ። ስደተኞቹ ገንዘብ ካለቀባቸው ልክ እንደባርያ በነፃ እንዲሰሩ ይደረጋሉ ። ለደላሎቹ ገንዘብ ክፍያ እንዲሆናቸው ማለት ነው። ወንዶቹ ከባድ የጉልበት ስራ እንዲሰሩ ሲደረግ ሴቶቹ ደግሞ በሴተኛ አዳሪነት እነዲሰሩ ይገደዳሉ።

የ2017 ዓ/ም የሲ.ኤን.ኤን የቪድዮ ዘገባ ተከትሎ የባርያ ንግድ ጨረታ በግላጭ በሊቢያ ከታዮ በኃላ ሰደተኞቹ በደላሎች በግልፅ ገበያ ላይ በሃገሪቱ እየተሸጡ መሆናቸው ዘገባዎች ቀጥለዋል።

የሰሃራ በርሀ በጣም ሰፊና መንግስት አልባ አከባቢ ሆኖ ወንጀለኞችና ወረበሎች ስደተኞች ላይ ጥቃት በማድረስና በማፈን ንብረታቶቻቸውን የሚዘርፉበት ቦታ ነው።

የበረሃው ጉዞ ሳምንታትን ሊወስድ ይችላል። የመልክኣ ምድራዊ አቀማመጡም አስቸጋሪና የሙቀት መጠኑም በቀን ከፍተኛ ስለሆነ መኪኖች እሰከ መበላሸት መሰበር ይደርሳሉ ፤ መኪኖች ሲበላሹ ወይም ሹፌር ሲሰወር ስደተኞች በረሃብና በውሃ ጥም ወይም በልብ ድካም ይሞታሉ። ትርፋቸውን ለማጋበስ ደላሎች ብዙ ስደተኞችን መኪናው ውስጥ አንድ ላይ በማጨቅ ለተጓዦቹ እግጅ አስገቻሪና አደገኛ ያደርጉታል።

በረሃውን የሚያቋርጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለዚህ አሰቃቂ ጥቃት ብቻ አይደለም የሚጋለጡት ፤ ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ወደ መዳረሻቸው እንዲያደርሳቸው ሳይሆን ለማፈንና ገንዘብ ለመቀበልም ያመቻቻሉ። በዚህ ጉዞ ወደ አውሮፓ ለመድረስ ኢትዮጵያውያን ብዙ ጊዜ ችግር አጋጥሟቸዋል

ስደተኞች በየጊዜው በሰሃራ በረሃ በጉዞ ላይ የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ይናገራሉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሬሳዎች በበረሃው ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙ ለመንግስት ዘገባዎች ይቀርባሉ። በሜዲተራንያን ባህር ከሚሞቱ ሰዎች ህገወጥ ስደተኞች በሰሃራ በረሃ ውስጥ የሚሞቱት እንደሚበዙ ይገመታል

በ2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ ኢትዮጵያና ሱዳን የጋራ ድንበራቸውን የሚቆጣጠሩ የተቀናጀ ወታደራዊ ሃይል እንዲያቋቁሙ ተስማምተዋል። ይህም ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተደረገ ጥረት ነው። ሱዳን ከሌሎች አጎራባች አገራት ተመሳሳይ የድንበር የድህንነት ጥበቃ ስምምነት ከሊቢያ ፣ ቻድና ኒጄር ጨምሮ አደርጋለች። ይህም ማለት በሱዳን በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል። ነገር ግን አንድአንድ ስደተኞች በሱዳን በኩል ለማለፍ ሲሞክሩ በሃገሪቱ አስደንጋጭ ችግርና ስቃይ ይደርሰባቸዋል። ለምሳሌነት ብንጠቅስ ሰደተኞች ሱዳን ውስጥ በህገ ወጥ ደላሎች ብዙ ስቃይና እንግልትና አስገድዶ መደፈር በሱዳናውያን ፖሊሶች ይደርሰባቸዋል ፤ ይህም የሚፈፀመው ከህገወጥ ደላሎች በመተባበር መሆኑ ነው።

ሊቢያ ያልተረጋጋችና ብዙ ተጠቂ ቡዱኖች ስደተኞችን በማፈን መያዠያ የሚያደርጉበት አገር ነች። እነዚህ ታጣቂ ቡዱኖች ስደተኞችን በማሰርና በማሰቃየት የማስለቀቅያ ገንዘብ ለስደተኞች ቤተሰቦች ከመጡበት አገር እንዲላክላቸው ይጠይቃሉ።

አብዛኛዎቹ ስደተኞች ሊቢያ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን አሳንሰው ይመለከቱዋቸዋል።  የሰሃራ በረሃን ማቋረጥ እጅግ ከባድና አስቸጋሪ እንደሆነ አይገነዘቡም። ሲፋር የተባለ ተመራማሪ የምዕራብ አፍሪቃ ስደተኞችን ተሞክሮ በማየት እንዳጠናውና ጥናቱ እንዳመለከተው ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ስደተኞች አካላዊ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ይተነትናል። ከኦክስፎም የተገኘው ሪፖርትም ሶስት አራተኛ የሚሆኑት ስደተኞችን ቃለ መጠየቅ በማድረግ በሊቢያ ያላቸውን ተሞክሮ ሲገልፁ ሰዎች  ሲሰቃዩ ወይም ሲገደሉ እንዳዩ ገልፀዋል።

በ2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ ከ 600 መቶ ሺ/ከስድስት መቶ ሺህ/ በላይ ስደተኞች ሊቢያ ውስጥ እንደነበሩና ከ 9 ሺ በላይ በመንግስት እስር ቤቶች (ማእከላት) ተይዘው እንደነበርና በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ደግሞ በታጣቂ ቡዱኖች በድብቅ ቦታ ተግተው እንደነበሩ የአለም አቀፍ የሰደተኞች ድርጅት ገልፀዋል።

እንደ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በ2018 ዓ/ም አውሮፓ ለመድረስ   ወደ 2300 ሰዎች በሜዲተራንያን ባህር ውስጥ ሰጥመው እንደሞቱ ወይም ደብዛቸው እንደጠፋ ይገለፃል። ህገወጥ ደላሎችና አዘዋዋሪዎች ስለጉዘውና የመንገዱ ርዝመት ይዋሻሉ። የጉዞ ጀልባዎችን በተመለከተም እንዲሁ ምቹና ጥሩ እንደሆኑ ይዋሻሉ ። ጀልባዎቹም ከአቅም በላይ ሰው ስለሚጫኑ የመስጠም አደጋ ያጋጥማቸዋል።

የለቢያ የጠረፍ ጥበቃ በመጠናከሩ በህገ ወጥ መንገድ የመዲተርያንያን ባህር ለማቋረጥ በሚሞክሩበት ጊዜ  በመሃል በጠባቂዎች ይያዛሉ ፤ ወደ ሊቢያም ይመለሳሉ።

በ2018 እ.ኤ.አ ቢያንስ 10 ሺ ሰዎች በሊቢያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች እንደተያዙና ወደ እስር ቤት እንደገቡም ታውቋል። የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችና ነፍስ አድን ሰራተኞች በአከባቢው ጥናት ሲያካሂዱ የነበሩ ቦታውን ለቀው መውጣታቸውና ይህም የስደተኞች የመሸጋገር ሙከራ የባሰ ተጋላጭ እንዳደረገው ይታመናል።

ለሌላ ያካፍሉ

የእንገሊዝ ቻናል በማቋረጥ ላይ ለነበሩ ስደተኞች ድጋፍ አድርጋቹኋል የተባሉ ሁለት ፈረንሳውያን ታሰሩ

ሁለት ፈረንሳውያን ስደተኞች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው ወደ እንግሊዘ እንዲገቡ በማገዛቸው ምክንያት በእስር እንዲቀጡ...
ተጨማሪ ያንብቡ

በፓሪስ አየር መንገድ ተርሚናል በሀይል ወደ ሀገር ቤት አንመልስም ያሉ በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሰለማዊ ሰልፍ አደረጉ

በመተዎች የሚቆጠሩ ህገ ወጥ ስደተኞች በፈረንሳይ መዲናዋ ፓሪስ ከተማ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ በመሰባሰብ...
ተጨማሪ ያንብቡ

የፈረንሳይ የባህር ላይ ጥበቃ ሀይሎች የእንግሊዝ ቻናል አልፈው ለመሄድ የሞከሩ ዘጠኝ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

መይ እሁድ 19 ቀን 2019 ዘጠኝ ስደተኞች በመያዝ በእንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ እንግሊዝ በመሄድ ላይ የነበረ ትንሽ ጀልባ...
ተጨማሪ ያንብቡ

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ