ለሴቶችና ህፃናት አደገኛ የሆኑ ሁኔታዎች

ከአፍሪካ ቀንድ እስከ አውሮፓ ድረስ ያለው ጉዞ በተለይ ለሴቶችና ህፃናት አደገኛ ነው።

አብዛኛዎቹ ሴቶችና ህፃናት በጉዛቸው ላይ አከላዊ ጥቃት ማለትም ስቃይ አስገድዶ የመደፈርና በባርነት የመያዝ እንዲሁም ሌሎች ስነልቦናዊ ስቃይና ጉስቁልና ይደርስባቸው።

ሕገወጥ ስደት በተለይ ለሴቶችና ልጃገረዶች አደገኛ ነው። ሕገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ኣብዛኛው ጊዜ ለሚሰጡዋቸው አገልግሎቶች በወሲብ እንዲከፍሉዋቸው ሴቶችን ያስገድዳሉ ። ሴቶችና ህፃናት  እንደየሁኔታውና በየቦታው በሚከፈል በህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ሴራ ላይ በመውደቅ አብዛኛው ገንዘብ የሚከፈለው በጉዞ ላይ ወይም በሚያርፉበት ቦታ ሲሆን ይህም በዕዳ እንዲያዙና በዚህም ምክንያት ለጥቃትና ለህገወጥ ዝውውር ሰለባ እንደሚሆኑ ዩኒሴፍ በ2017 እ.ኤ.አ ባደረገው ጥናት አረጋግጧል።

በሊቢያ ጥናት ከተደረገላቸው ግማሽ የሚሆኑት ህገ ወጥ ሴቶችና ህፃናት ስደተኞች በጉዛአቸው ወሲባዊ ጥቃትና ስቃይ እንደደረሰባቸው በጥናቱ ተረጋግጧል። በኢትዮጵያ አብዛኛዎቹ ሴቶችና ልጃገረዶች ስደተኞች የምድረበዳውን ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የእርግዝና መከላከያ መርፌ እንዲወጉ ይደረጋል። ይህም የሚሆንበት ምክንያት በጉዞአቸው አደገኛ የመደፈር ሁኔታ ስለሚያጋጥማቸው ነው።

አውሮፓ ከደረሱ በኃላም በማስተናገጃ ማእከሎች ፣ በእስር ማቆያ ማእከሎች ፣ በጊዚያዊ ማረፍያ ቤቶች ከፍተኛ የሆነ የጭንቀትና ጥቃት እንደሚደረሳቸው ሴቶቹ ይናገራሉ። አብዛኛው ጊዜ ለጥቃት  ተጋላጭ የሆኑትን ሴቶች ሰደተኞች ማግኘት የሚገባቸውን የተለየ እገዛ አይደረግላቸውም። ለምሳሌ እርጉዝ ሴቶች የጤና እንክብካቤና መደበኛ ምርመራ ለማግኘት ይቸገራሉ። ንፅህና የሌለው የኑሮ ሁኔታም እርጉዞቹ ለተወሳሰቡ አደጋዎችን እንዲጋለጡ ያደርጋል።

ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በሚያደርጓቸው ሕገወጥ የስደት ጉዞዎች ለአደጋ እጅግ ተጋላጭ ናቸው። እነዚህ ልጆች ወደ አውሮፓ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ሞት ጥቃትና ብዝበዛ እንደሚደርስባቸው የተመዘገቡ መረጃዎችን ያመለክታሉ። አለም አቀፍ የስደተኞች ፅ/ቤት ድርጅት በጣልያን ውስጥ ካሉት 4700 ስደተኞች በላይ 77% ያለ ፍቃዳቸው በግድ በሊቢያ ተይዘው እንዲቆዩ መደረጋቸውን በጥናቱ አርጋግጧል።

እነዚህ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ብቻቸውን አውሮፓ ሲደርሱ አብዛኛዎቹ ይጠፋሉ ። ልጆቹ በተደራጁ የወንጀለኞች ቡዱን ተይዘው የወሲብና በህፃናት የጉልበት ስራ ብዝበዛ ተጠቂዎች ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይታሰባል።

ለሌላ ያካፍሉ

የእንገሊዝ ቻናል በማቋረጥ ላይ ለነበሩ ስደተኞች ድጋፍ አድርጋቹኋል የተባሉ ሁለት ፈረንሳውያን ታሰሩ

ሁለት ፈረንሳውያን ስደተኞች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው ወደ እንግሊዘ እንዲገቡ በማገዛቸው ምክንያት በእስር እንዲቀጡ...
ተጨማሪ ያንብቡ

በፓሪስ አየር መንገድ ተርሚናል በሀይል ወደ ሀገር ቤት አንመልስም ያሉ በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሰለማዊ ሰልፍ አደረጉ

በመተዎች የሚቆጠሩ ህገ ወጥ ስደተኞች በፈረንሳይ መዲናዋ ፓሪስ ከተማ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ በመሰባሰብ...
ተጨማሪ ያንብቡ

የፈረንሳይ የባህር ላይ ጥበቃ ሀይሎች የእንግሊዝ ቻናል አልፈው ለመሄድ የሞከሩ ዘጠኝ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

መይ እሁድ 19 ቀን 2019 ዘጠኝ ስደተኞች በመያዝ በእንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ እንግሊዝ በመሄድ ላይ የነበረ ትንሽ ጀልባ...
ተጨማሪ ያንብቡ