ኢትዮጵያውያንና ኤትራውያን ስደተኞችና የአውሮፓ ኑሮ

ብዙዎች ሕገ ወጥ ስደተኞች ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ / የወደፊት ህይወታቸውን የተሻለ ለማድረግ/ ከአፍሪቃ ቀንድ ወደ አውሮፓ ይሰደዳሉ።  ሆኖም ግን አብዛኛውን ግዜ ስደተኛች ከሚያስቡት እውነታ የተለየና አብዛኛዎቹ አውሮፓ ከደረሱ በሃላ ስለሚያጋጥሟቸው መሰናክሎች ግንዛቤ  የላቸውም።

ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ የገባህ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኛ ሰለ የአውሮጳ ኑሮ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን ማንበብ ይገባል።

ጥገኝነት ጠያቂ የሚባለው   ጭካኔና ሚዛናዊ ባልሆነ መንገድ ከፍ ያለ ጉዳት ሲደርስበት አገሩን ጥሎ ወደ ሌላ አገር በመሸሽ አለም አቀፋዊ ጥብቄና የስደተኝነትን ጥገኝነት ለማግኘት ሲል የሚጠይቅ ወይም የሚያመለክት ሰው ማለት ነው። በዚህ  መረጃ ስለ ጥገኝነተን ጠያቄዎችና ስለሌሎች የስደት ቁልፍ ማብራሪያዎች በበለጠ ለመገንዘብ ያስችላል።

በአውሮፓ የጥገኝነት ሁኔታዎች እንደ የአገሩ ብሄራዊ ሕግ ይለያያል። ሆኖም ግን የአውሮፓ ህበረት የጥገኝነት ሕግ እያንዳንዱ የአውሮፓ ህበረት ኣባል አገር የጥገኝነት ጠያቄዎች መብት እንድታከብር አጥብቆ ይደነግጋል።  ይህም ማለት እያንዳንዱ ጥያቄ አቅራቢ ሚዛናዊ የሆነ የጥገኝነት ማመልከቻ ሂደት የማግኘት መብት የተጠበቀ  ሆኖ አገሮቹ  ጥገኝነት ጠያቄዎች ማረፍያ ቦታና መሰረታዊ ነገሮች እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። ለየአንዳነዴ የጥገኝነት ጠያቄዎች ምክንያት ቫውቸር / እንደገንዘብ ሆኖ የሚያገለግል ወረቀት/ አንዳንዴም ገንዘብ ይሰጣሉ።  

በአውሮፓ ህብረት ጥገኝነት የማግኘት እድሎቹ እንደየ አገሩና እንደጠያቂው ሁኔታ ይለያያል።

ይሁን እንጂ የአውሮጳ ህብረት ሕግ የጥገኝነት ጠያቂ መብት መከበር አለበት ነው የሚለው፡፡ ይህ ማለት ማነኛውም ጥገኝነት ጠያቂ ጉዳዩ በትክክለና አሰራር እንዲያልፍና ውሳኔ እስከሚሰጠው ግዝያዊ መጠለያና መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲቀርቡልት ያስገድዳል፡፡ በአንዳንድ  አጋጣሚ ደግሞ ለጥገኝነት ጠያቂዎች ትንሽ የኪሰ ገንዘብ ይሰጣቸዋል፡፡

አንድ ጥገኘነት ጠያቂ ኢትዮጵያዊ ጥያቄው ተቀባይነት ሊኖሮውም ላይኖሮውም እንደየአገሩ ልለያይ ይችላል፡፡ ከዚህ ውጭ የስደተኛው የመሰደድ ምክንያት እርግጠኛ እንዲሆን አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ ፈረንሳይ 2017 .. በግምት 600 ከሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ከቀረቡላት አዳዲስ የጥገኝነት ማመልከቻዎች መካከል ግማሹን ያህል ተቀብላለች። በተመሳሳይ አመት ጎረቤትዋ የሆነችው ቤልጂየም ግን 85 አዳዲስ አመልካቾች መካከል 20 ሰዎች ብቻ ተቀባይነት እንዲያገኙ አድርጋለች። 

የደብሊን መተዳደርያ ደምብ ተብሎ የሚጠራው የአውሮፓ ህብረት ህግ ማለት  ጥገኝነት ጠያቄዎች በመጀመርያ በገቡበት የአውሮፓ አገር ውስጥ ሃላፊነት ወይም ተጠያቄነት ስር ናቸው። ይህም ማለት ወደ አንድ የአውሮፓ አገር ከደረሱ በሃላ ወደ ሌላ አገር ከተንቀሳቀሱ ተይዘው መጀመርያ ወደ ገቡበት አገር ይመለሳሉ።  በተጨማሪም የደብሊን መተዳደርያ ደምብ ማለት ጥገኝነት ጠያቄዎች በየተኛው ቸግር እንደሚኖሩ የተኛው ቸገር የጥገኝነት ጥያቄኣቸው እንደሚመረምረና በዛችም አገር በየተኛው ቦታ እንደሚቀመጡ ምርጫ አይሰጣቸውም። 

የጥገኝነት ጥያቄ / ማመልከቻ ሂደት ረጅም ግዜ ሊወስድ ይችላል። ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ አገሮች ጉዳዩን በስድስት ወራት ውስጥ እልባት እንዲያገኙ የሚያደርጉ ቢሆኑም፤ ከፍተኛ የጥገኝነት ጥያቄዎች/ ማመልከቻዎች በሚበዙበት ሁኔታ ይህን ግዜ ያራዝሙታል።

የጥገኝነት ማመልከቻዎች ከባድና ውስብስብ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንድ አመልካቾች ጥያቄአቸው ተቀባይነት ሲያገኝ የአብዛኛዎቹ ሌሎች ደግሞ ተቀባይነት አያገኙም። ይህም ማለት ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ ሲደረግ ወድያን አገሩን ለቀው እንዲሄዱ ይነገራቸዋል። አንዳንዴም ወደ መጡበት አገር እስኪመለሱ ድረስ በእስር ቤቶች እንዲቆዩ ይደረጋሉ። ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አመልካቾች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ የማለት መብት አላቸው። ተቀባይነት ያገኙ ጥያቄቸው እንደገና ከመታየቱ በፊት የመኖርያ ፍቃድ በማግኘት ለተወሰኑት ጊዜ እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡

የኢኮኖሚ ጥገኛ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ለማሻሻል ወደ ሌሎች አገሮች ይሰደዳሉ።የኢኮኖሚ ስደተኞች ለተሻለ ኑሮ በፍቃደኝነታቸው የሚሰደዱ በመሆናቸው የጥገኝነት ጥያቄ እንድያቀርቡ መበብት የላቸውም፡፡ በሕገ ወጥ መንገድ  ወደ በአውሮፓ ከገቡ በሃላም እስራትና መባረርም ይጠብቃቸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ የኢኮኖሚ ስደተኞች በአውሮፓ ውስጥ የተሻለ ገቢ/ገንዘብ ይግኛል ብለው  በማመን ወደ ስደት ያመራሉ። ሆኖም ግን ወድያውኑ ስራ ለማግኘት ስለሚቸገሩ ወደ እዳ ይገባሉ፡፡ አገር ቤት የተዋቸውን ቤተሰብ ማስተዳደር አይቸሉም፡፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ ስድተኞች ስራ በማግኘት ስኬታማ ቢሆኑም አብዛኛዎቹ ግን አይሳክላቸውም።  በአውሮፓ ያለው የቅጥር ሁኔታ በጣም ህግን የተከተለ  ነው፡፡ ስራ ፈላጊዎች ተቀጥረው ለመሰራት ህጋዊ ማሰረጃዎች እንደነ ፓሕጋዊ ስፖርቶት መታወቅያ ወረቀት፣ የትምህርት መረጃዎች፣ እንዲሁም መስራት እንደምትችል ፍቃድ ያገኘህ መሆን እንደታቀርብ ትገደዳለህ ፡፡ ካምፓኒዎች ህጋዊ የስራ ፍቃድ የሌላቸውን ሰዎች ከቀጠሩ ወንጀል ነው፡፡  የልዩ ህግ አስከባሪ ወኪሎች ህጋዊ ያልሆኑ ሰራተኞች እንዳይቀጠሩ በካምፓኒዎች ላይ መደበኛ ቁጥጥር ያደርጋሉ።

በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ያለው የስራ አጥነት ቁጥር በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡  በተለይ ዝቅተኛ የስራ ልምድና ትምህርት ወይም ብቃት ባላቸው ወጣቶች ላይ በጣም የላቀ ነው። አብዛኛው ግዜ ስደተኞች በአገራቸው ካለው የስራ አይነት  በአውሮፓ ውስጥ የሚጠብቀቸው የስራ በህሪና አይንት  የተለየ ስለሆነ ባገኙት ሰራ ተወዳዳሪዎች ለመሆን ይቸገራሉ፡፡ስራ ለማግኘት አስፈላጊውን ችሎታ ወይም ብቃት የላቸውም። ከባህር ማዶ ከአገራቸው ይዘውት የመጡ ችሎታ በቀጣሪዎቻቸው ዘንድ ተቀባይነት አያገኝም። ስራን ለማግኘት የሚኖርበትን አገር ቋንቋ መናገር ነፃፍ ያስፈልጋል።

ምንም እንኳን በአውሮፓ ያለው የክፍያ መጠን ከአብዛኛው የስደተኞች አገር ጋር ሲነፃፀር የላቀ ቢሆንም፤ የኑሮ ውድነት ደግሞ በጣም የላቀ ነው። በአውሮፓ ለእለት ኑሮ ለመኖርያ፣መጓጓዣና ምግብ የሚደረገው ወጪ በጣም ውድ ነው። ለምሳሌ 2018 .. በዩናይትድ ኪንግዶም አንድ አባወራ  ማለት ቤተሰብ አስተዳዳሪ በሳምንት በአማካይ 730 የኤሜሪካ ዶላር ወጪ አድርጓል በሕገ ወጥ ስደት ምክንያት የሚያጋጥሙትን ገንዘብ ነክ ጉዳቶች ከዚህ መረጃ መገንዘብ ትችላላችሁ።

በሕገ ወጥ ስደት ምክንያት የሚያጋጥሙትን ገንዘብ ነክ ጉዳቶች ከዚህ  ትችላላችሁ።

በአውሮፓ ህግ መሰረት ጥገኝነት ጠያቂዎች ጥያቄአቸው ምላሽ እስከሚያገኝ መኖርያ ቤት መብታቸው ነው፡፡  ምንም እንኳን እንዲህ በመደረጉ በገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ እፎይታ ቢያስገኝም፤ ስድተኞች ሌሎች መሰናክሎች ያጋጥማቸዋል። ጥገኝነት ጠያቂዎች በየት መኖር እንደሚፈልጉ ምርጫ አይሰጣቸውም። አብዛኛወ ግዜ ከቦታ ወደ ቦታ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል። አንዳንደቹ ራቅ ባለ ቦታና በዙ ነዋሪ ህዝብ በሌለበት ጎጦች እንዲኖሩ ስለሚደረግ ብዙ ስደተኞች በከባድ ብቸኝነትና አእምሮአዊ ቀውስ ይወድቃሉ፡፡የጥገኝነት ጥያቄአቸው ተቀባይነት ካገኘም ያለ ክፍያ ይኖሩበት ከነበረ መኖርያ እንዲወጡና ንሮአቸውን ራሳቸው እንዲመሩ ሰለሚደረግ ችገሩ እንደገና ከባድ ይሆናል፡፡

 ሕገ ወጥ ስደተኞች ምንም የሚያገኙተ መጠልያ ይሁን ሌላ ማህበራዊ አገልግሎቶች የለም፡፡ ይህም ማለት ወደ አውሮፓ ከገቡበት ግዜ ጀምሮ በራሳቸው የሚቆይበትን ቦታ የማግኘት ሃላፊነት አለባቸው። በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች የጋራ መኖርያ ቤቶች እጥረት ስላለባቸው ስደተኞች የግል መኖርያ ቤቶች ይከራያሉ። ይህም ኪራይ ውድ በመሆኑ አስፈላጊውን አቅርቦት የሌለው ቤት  ብውድ ዋጋ ተከራይተው በመክፈል ለአካራይዎቻቸው ብዝበዛ ይጋለጣሉ።

ሕገ ወጥ ስደተኞች ማረፍያ ቤት ለማግኘት የሚደረግላቸው እገዛ የለም። ይህም ማለት ወደ አውሮፓ ከገቡበት ግዜ ጀምሮ በራሳቸው የሚቆይበትን ቦታ የማግኘት ሃላፊነት አለባቸው። በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች የጋራ መኖርያ ቤቶች እጥረት ስላለባቸው ስደተኞች የግል መኖርያ ቤቶች ይከራያሉ። ይህም ኪራይ ውድ በመሆኑ አስፈላጊውን አቅርቦት የሌለው ቤት ብውድ ዋጋ ተከራይተው በመክፈል ለአካራይዎቻቸው ብዝበዛ ይጋለጣሉ።

ብዙ ሰደተኞች ወደ አውሮፓ በሚያደርጉት አደገኛ ጉዞ ጤንነታቸውና ደህንነታቸው አደጋ ውስጥ ይከታሉ/ይጥላሉ። ወደ አውሮፓ ከሚገቡት ህገወጥ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች አብዛኛዎቹ የህክምናና የሰነልቦና እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። 

ጥገኝነት ጠያቂዎችና ህገወጥ ስደተኞች በብዙ የአውሮፓ አገሮች ነፃ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ይቸገራሉ። ህገ ወጥ ስደተኞች ነፃ ህክምና ማግኘት የሚችሉት ለአስቸኳይ /አጣዳፊና ለህይወት አስጊ ለሆኑ ህመሞች ብቻ ነው። ይህ ካልሆነ ግን የህክምና እርዳታ ለማግኘት መክፈል ያለባቸው ሲሆኑ ዋጋውም ከፍተኛ ገንዘብ ሊሆን ይችላል።

በአውሮፓ ብዙውን ጊዜ የዩኒቨርስቲ ትምህርት በነፃ አይደለም። ከፍተኛ ብቃትና ተወዳዳሪ የሆኑት ስደተኞች ነፃ የትምህርት እድል ልያገኙ ይችላሉ፡፡ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት እድል በአውሮጳ  ባለመኖሩ ብዙ ስደተኞች በቂ ብቃትና የትምህርት ደረጃ ይዘው ከፍ ያለ ደመዎዝ ልያገኙበት ወደሚችሉበት ስራ ማግኘት አይችሉም፡፡ስለሆነም ብዙ ስደተኞች ወደ ከባድ የንሮ ችግር ይወድቃሉ፡፡ ከዚህ መረጃ ዋስትና ያለው ሕጋዊ አማራጮችን ለማወቅ ትችላላችሁ።

ቀደም ብሎ በአገራቸው ውስጥ እያሉ  የተማሩት የስደተኞች ሙያን የሚጠይቅ ስራ ለማግኘት ሲፈልጉ አገራቸው ከሚገኙት የትምህርት ተቋሞች ህጋዊ በማስረጃ የተረጋገጠ የትምህርት መረጃ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። አንዳንድ ስራ ቀጣሪዎች ለሙያው እውቅና አይሰጡትም። ሆኖም ግን ስድተኞች የሙያቸውን መረጃ በሌላ ቋንቋ እንዲተረጎምና ተቀባይነት እንዲያገኝ ገንዘብ መክፈል ይኖርባቸዋል። 

ስደተኞች ከማያውቁት የአውሮፓ ማህበረሰብ ጋር ለመቀላቀል ከባድ ችግር ነው የሚሆንባቸው፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ስደተኞች በአውሮፓ ያለውን አዲስ ህይወት ቢለማመዱትም ሌሎች ደግሞ በቋንቋዎችና ባህላዊ ልዩነት ምክንያት ከአካባቢው ማህበረሰብ በአጭር ግዜ እንዲቀላቀሉ ይቸገራሉ፡፡ ሌሎችም ከአንዳነድ አውሮጳውያን በሚደርሳቸው ዘርን መሰረት ያደረገ አመለካት ስለሚሰማቸው ብቸኝነት ይመርጣሉ፡፡ ብዙ ስደተኛ ቤተሰቦች ለአገራቸው ባህል ያላቸው ከፍተኛ ዋጋ በመጠበቅ ከአዲሱ ባህል ጋር ለመቀላቀል አስቸጋሪ ነገር ሆኖባቸዋል፡፡

ብዙ ሕገ ወጥ ስደተኞች አውሮፓ ከገቡ በሃላ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ በመደረጉ ያለ ህጋዊ ቪዛ አውሮፓ በመግባታቸው ምክንያት በፀጥታ አካላት ተይዘው ወደ አገራቸው ሊመለሱ ይችላሉ።

ከስደት ተመላሾች ወደ አገራቸው ከገቡ በሃላ በአገራቸው የተለያዩ ችገሮች ነው የሚያጋጠማቸው፡፡.

የሕገ ወጥ ስደት ሙከራ ካልተሳካ ስደተኞች በፀፀት ይሞላሉ። ለማይሳካ ጉዞ ጊዜና ገንዘብ ማባከናቸው ምክንያት ከዘመዶቻቸው ቁጣ እንደሚደርሰባቸው ይናገራሉ።። አንዳንዶቹ ደግሞ በቤተሶቦችና በአከባቢው ህበረተሰብ እንደ ሰነፍ ይቆጠራሉ፡፡በተለይ በስደት ረጂም አመታት ቆይተው ለተመለሱ ከባድ ችግር ይሆናል፡፡

ስደተኞች በፈረንሳይ

በአሁን ሰዓት በፈረንሳይ ሀገር በህገ ወጥ ስደተኛነት ይኖራሉ? በሌላ አነጋገር...
ተጨማሪ ያንብቡ

ህይወት በእንግሊዝ ሀገር

በህገ ወጥ መንገድ ወደ እንግሊዝ ሀገር ለመሄድ አስበው ይሆናል። ይሁንና ወደ...
ተጨማሪ ያንብቡ
ለሌላ ያካፍሉ