ሰደትን የሚመለከቱ ቃላት ቁልፍ መመሪያ (መፍቻ)

ሰዎች ኢትዮጵያ  ትተው እንዲሰደዱ የሚያደርጓቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ። ለምሳሌ አንዳንዶቹ የበለጠ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት (እድል) ፍለጋ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በአውሮፓ ጥሩ ኑሮ ለመመሰረት (ለመገንባት) ነው።

አንተ ለመሰደድ እያሰብክ ነውወይስ ተሰደህ ውጥተሃል? እንዲህ ከሆነ ሰደትን በሚመለከት ለማወቅ የሚረዱህና መብትህን አውቀህ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንድታደርግና ለስደትና ስደተኞችን የሚያመለክቱ ቃላት እንድትገነዘባቸው አስፈላጊ ነው።

እንደ አለም አቀፍ የሰደተኞች ድርጅት (አይ..ኤም) አተረጓጎም ስደተኛ የሚባለው ማንኛውም ሰው የአለም አቀፍ ድንበርን ተሻግሮ እየሄደ ያለና ወይም አለም አቀፍ ድንበር ተሻግሮ የተጓዘ ወይም በሃገር ውስጥ ከመንግስት አስተዳደር ወሰን ርቆ መኖሪያ ቦታውን/ዋን የለቀቀ ማለት ነው። ይህንን መግለጫ የሚያሟላ ህጋዊነቱ ምንም ይሁን ምን በራሱ ነፃ ምርጫም ይሁን በሌላ ከአገር ወይ ከመኖርያው ከራቀ የሚያገኘው የአጠራር መብት የተሰደደበት ምክንያትም የሆነ ይሁን ስደተኛ ነው።

ህገወጥ ስደተኛ የሚባል ካለ ምንም ዓይነት ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችና የተፈቀደ ቪዛ ወደ አንድ ሃገር የገባ ማለት ነው። እስር ቤት እንዳይገቡና ወደ መጡበት የትውልድ ሃገር እንዳይመለሱ ህገወጥ ስደተኞች አብዛኛው ጊዜ ወደ ሃገር የሚገቡት መንግስት በሚያውቃቸው የመግቢያ በሮች (ኬላዎች) እንዲሆን አይመርጡም

በሌላ በኩል ደግሞ ህጋዊ ስደተኛ (ተጓዥ) የሚባለው ሁሉንም የጉዞ ሰነዶች አሟልቶና የመግቢያ ፈቃድ ቪዛና ሌሎችም አስፈላጊ ፍቃዶች ይዞ (ለስራ ለመኖርያ ለትምህርት ወዘተ) በፈቃድ ወደ ሃገር የሚገባ ማለት ነው። እነዚህን ሰነዶች አሟልቶ በመቅረብ በሕጋዊ የመግቢያ በሮች (ኬላዎች) በኩል ሲመጣና በመግቢያ በር ሃላፊዎች እንዲገባ ሲፈቀድለት ሕጋዊ ሰደተኞች ይባላል።

ጥገኝነት (ተገን) ጠያቂ የሚባል፤  የትውልድ አገሩን ትቶ (በመሸሽ) እንዳይታሰር እንዳይሰቃይና እንግልት እንዳይደርስበት በመፍራት (በመስጋት) ወደ ሌላ አገር በስደት የገባና አለም አቀፍ ከለላና ጥገኝነት በሌላው አገር የሚጠይቅ ሰው ማለት ነው። 

ማነኛውም ጥገኝነት (ከለላ) ጠያቂ  1951  በተ.. በተደረገው የስደተኞች ስምምነት መሰረት ከለላ ይሰጣቸዋል። ስምምነቱ እንደሚያስረዳው ምንም እንኳን በህገወጥ መንገድ ወደ አንድ አገር ቢገቡም ጥገኝነት ጠያቂዎች ፍትሃዊ የሆነ የተገን ጥያቄ ሂደትና እርምጃዎች ማግኘት አለባቸው። ለጥያዌአቸው ተገቢው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ደህንነታቸው ተጠብቆ መቆየት አለባቸው። 

የጥገኝነት ጠያቂ ማመልከቻ ውድቅ የተደረገ እንደሆነ ከአገሪቱ እንዲወጡ ይገደዳሉ፡፡ ወደ ሌላው አገር በህገወጥ መንገድ የሚገቡ ሌሎች ስደተኞችም በአገሪቱ ሊያቆያቸው የሚችል ፍቃድ ከተከለከሉ ተመሳሳይ እጣ ይጠብቃቸዋል፡፡

ጥግተኞች ለህይወታቸው የሚፈታተኑ በአገራቸው ያሉ ጦርነትን ብዝበዛ በመሸሽ በሌላ አገር ጥገተኝነት የሚጠይቁና ጉዳያቸው ተቀባይነት ካገኘ የጥግተኝነት ሙሉ መብት የተሰጣቸው ሰደተኞች ናቸው፡፡አንድ ሰደተኛ እንደ ጥግተኛ ተቀባይነት የሚያገኝ ከሆነ  በትውልደ አገሩ በዘሩ፣በሃይማቱ፣ በፖለቲካዊ እንቅስቃሴው ምክንያት ሊደርሰው የሚችል የሚያሰጋ ነገር እንዳለ መታመን አለበት፡፡

ጥግተኞች የጥግተኝነት ጥያቄአቸው በተቀበለች አገር ላልተወሰነ ግዜ በአህጉራዊ ዋስትና ስር በሰላም እንዲኖሩ ይፈቀደላቸዋል፡፡

ጥግተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሃገሪቱን ለቀው የወጡበት ምክንያት ጦርነትና ስጋት የሸሸ ሲሆ፤  የኢኮኖሚ ስደተኞች ግን ሃገራቸውን ለቀው የወጡበት ምክንያት የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻልና በራሳቸው መልካም ፍቃድ የሚሰደዱ ነው።  የኢኮኖሚ ስደተኞች ለተሻለ ኑሮ በፍቃዳቸው የሚሰደዱ ማለት ነው፡፡  እነኝህ  ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሌላ አገር ቢገቡም ይታሰራሉ።  ወደ አገራቸውም እንዲመለሱ (እንዲባረሩ) ይደረጋል። 1951 ..  በተ.. የስደተኞች ስምምነት ሰነድ መሰረት የኢኮኖሚ ስደተኞች አይስተናገዱም። 

የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ የሚባለው በአንድ አለም አቀፍ ድንበር (ወሰን) ውስጥ የትውልድ ስፈራውን (ቀየውን) ጥሎ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄድ የተገደደ ሰው ማለት ነው። ቀየውን የለቀቀበት ምክንያት የርስ በርስ ውጊያ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ወይም በአደጋ (ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ) ሊሆን ይችላል። 

ብቸኛ ህፃን (አሳዳጊ የሌለው) ህፃን ስደተኛ ሞግዚት አልባ ስደተኛ የሚሉት ቃላት በተመሳሳይነት ለህፃን ስደተኞች እንጠቀምባቸዋለን። እነዚህ ቃላት ከእድሜ በታች ለሆኑት (18 ዓመት በታች ለሆኑት ህፃናት ተንከባካቢ (ሞግዚት) የሌላቸው ህፃናት እንጠቀማለን። በየ.. የህፃናት መብት ተሟጋች እንደሚገልፀው ህፃን ማለት የሰው ልጅ (ዘር) ሆኖ 18 ዓመት በታች ለሆነ ብቻ ነው። 

የድንበር (ወሰን) አስተዳደር ማለት በድንበር የሚታይ ሁሉም ፖሊሲዎች ህጎችና የህዝብ ጉዳዮች የሚያሳልጡ ወይም የሚያደናቅፉ በህግ የተፈቀዱ የውጭ ጉዞዎች /ለንግድ ለስራ ለትምህርት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል ጥገኝነት ለመጠየቅ) ወዘተ እና ሌሎች የህዝብ እንቅስቃሴዎች (ለጉብኝት ቱሪዝም ቤተሰብ ጥየቃ ለአጭር ጊዜ ስራ ለንግድ ጉብኝት ወዘተ ወደ አንድ ሃገር መጓዝ ማለት ነው።  የድንበር አስተዳደር ሃላፊዎች ዋና አላማቸው ህገወጥ ዝውውርን መቆጣጠር እና ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከላከል ነው።

ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ማለት አንድን ሰው በህገ ወጥ መንገድ በሃገር ውስጥ ወይም ድንበር አከባቢ ለብዝበዛ ሲባል የሚደረግ የሰዎች ዝውውር ሲሆን ፤ የዚሁ ሰለባ የሚባለው ሰው ደግሞ በማስፈራራት ፣ በማፈን ፣ በማታለልና ያልተገባ ክፍያ እንከፍልሃለን በሚል አጉል ተስፋ በአዘዋዋሪዎች የተበደለ ነው ማለት ነው።

ሰዎች በህገወጥ መንገድ ከአንድ ስፍራ (ሃገር) በድንበር በኩል እንዲወጡ ቦታ በማሳየትና በማሻጋገር መርዳት (መተባበር) ማለት ነው። ህገወጥ ደላሎች ሰዎችን ድንበር አቋርጠው ከሃገር እንዲወጡ ማገዝ ራሱ ወንጀል መሆኑ መታወቅ አለበት።

ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ማለት አንድን ሰው በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ወደ አገር   ለብዝበዛ ሲባል የሚደረግ የሰዎች ዝውውር ነው፡፡ የዚሁ ሰለባ የሚባለው ሰው ደግሞ በማስፈራራት በማፈን በማታለልና ያልተገባ ክፍያ እንከፍልሃለን በሚል አጉል ተስፋ የአዘዋዋሪዎች እና የሰዎች ነጋዴ ሰለባ  ሆነ እንላለን። 

ሕገ ወጥ ዝውውር ግን በህገወጥ ደላሎችና አሸጋጋራች በስደተኞች ፍላጎት የሚካሄድ የስደት ጉዞ ነው፡፡አሸጋጋሪዎች ለስደተኞች ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ወደ ሚፈልጉት አገር እንዲገቡ ያግዛሉ እንጂ በስደተኞች ላይ  ማነኛውም አካላዊ ጉዳትና ብዝበዛ አያደርሱም፡፡  ህገወጥ ደላሎች ሰዎችን ድንበር አቋርጠው ከሃገር እንዲወጡ ማገዝ ራሱ ወንጀል መሆኑ መታወቅ አለበት።

የትውልድ አገር ማለት ሰዎች ወደ ስደት ከማመራታቸው በፊት የሚኖሩባት የማንነታቸው ቦታ ማለት ነው፡፡

የመሻጋገሪያ ሃገራት የሚባሉት ስደተኞች በጉዘአቸው ወቅት የሚያልፉባቸውና ወደ መዳረሻቸው አገር እስከሚደርሱ ለአጭር ግዜ ለማቆያ የሚጠቀሙበት አገሮች ናቸው፡፡ ለመሄድ ሲያስቡ ማለት ነው። በመሸጋጋሪያዋ አገር ለቀናት ወራት ወይም አመታት አንዳንዴም ያሰቡበትን አገር ላይደርሱ በመሸጋገርያ ሊኖሩ ይገደዳሉ። 

የመዳረሻ አገር ማለት ስደተኞች የጉአዘቸው መጨረሻና መኖርያ ብለው የሚያስቡት አገር ነው። አብዘኛዎቹ ስደተኞች የመዳረሻ አገር ብለው ያሰቡት አገር አይደርሱም መሸጋገሪያ አገር ብለው ያሰቡት አገር ይኖራሉ ወይም ተስፋ ቆርጠው ወደ ትውልድ አገራቸው ይመለሳሉ። 

ለምሳሌ አንድ ኤርትራዊ አገሩን ለቆ የሚዲተራንያን ባህርን አቋርጦ ጣልያን አገር ለመደረስ ሲፈልግ መጀመርያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ሊብያን ማለፍ አለበት፡፡በዚህ ሁኔታ የስደተኛው የትውልድ አገር ኤርትራ  ስትሆን የመዳረሻ አገር ደግሞ ጣልያን ናት ሱዳንና ሊቢያ ደግሞ የመሸጋገሪያ ሃገሮች ማለት  ናቸው።

ከስደት ተመላሽ የሚባለው ከተሰደደበት አገር ወደ ትውልድ አገሩ የተመለሰ ሰው ማለት ነው፡፡ 

በፈቃደኝነት መመለስ ማለት ስደተኛው ወደ ትውልድ አገሩ በመመልስ ህይወታቸው ሊመሩ የመረጡ ሰደተኞቹን ያመለክታል፡፡  በገዛ ፈቃድ መመለስ በትብብር ወይም በራሱ ሊደረግ ይችላል። በመንግስታት ትብብር መመለስ ይቻላል፡፡ በመንግስታት ትብብር ሲሆን  ተመላሾች የአስተዳደር የእቃዎች አቅርቦት የገንዘብ ድጋፍና ወደ ቤተሰብ የማገናኘት ስራ ሊያገኙ ይችላል። 

በአስገዳጅነት መመለስ ማለት ወደ ስደተኛው የትውልድ አገር በሃይል ሳይወድ በግድ ወይም ወደ ሌላ ሶስተኛ አገር የሚደረግ የመመለስ ስራ ነው። 

አስገድዶ ከአገር ማስወጣት መመለስ (የአስተዳደር ወይም የፍትህ ስራ ነው። ከአገር የማባረርና የማስወገድ ስራ የማስወገድ ስራ የእገድዶ መመለስ አካል ነው።

ከቤተሰቦች ጋር መቀላቀል (ማገናኘት) የማንኛውም ጥገኝነት ጠያቂ በጦርነት ጊዜ የተማረከ (ምርኮኛ) ወይም የሲቪል እስረኛ ወደ ትውልድ (የዜግነት) አገራቸው መመለስ የሚያስችል መብት ነው። ይህ የስደተኞ የመመለስ  ሰራ አለም አቀፍ ባለ ስልጣናትም በአለም አቀፍ ግጭት ጊዜ ይጨምራል። 

ወደ ሌላ አገር አሳልፎ መሸኘት (መመለስ) ማለት አንድን ስደተኛ ወደ ሌላ ቦታ (ሃገር መላክ ማለት ነው አብዛኛው ጊዜ ወደ ሌላ ሶስተኛ አገር መላክ ማለት ሲሆን ይህም የሰወቹን ደህንነትና ዋስትና በመሰጠት ከፍርሃትና ከእስር (ስቃይ) እንዲጠበቁ በማድረግ ነው። ተላልፈው የሚሰጡት ሰዎች ተቀባዩ አገር የረዥም ጊዜ የመኖርያ ፈቃድና መብር ሲሰጣቸው መሆኑ ተረጋግጦ ነው።

ለሌላ ያካፍሉ

የእንገሊዝ ቻናል በማቋረጥ ላይ ለነበሩ ስደተኞች ድጋፍ አድርጋቹኋል የተባሉ ሁለት ፈረንሳውያን ታሰሩ

ሁለት ፈረንሳውያን ስደተኞች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው ወደ እንግሊዘ እንዲገቡ በማገዛቸው ምክንያት በእስር እንዲቀጡ...
ተጨማሪ ያንብቡ

በፓሪስ አየር መንገድ ተርሚናል በሀይል ወደ ሀገር ቤት አንመልስም ያሉ በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሰለማዊ ሰልፍ አደረጉ

በመተዎች የሚቆጠሩ ህገ ወጥ ስደተኞች በፈረንሳይ መዲናዋ ፓሪስ ከተማ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ በመሰባሰብ...
ተጨማሪ ያንብቡ

የፈረንሳይ የባህር ላይ ጥበቃ ሀይሎች የእንግሊዝ ቻናል አልፈው ለመሄድ የሞከሩ ዘጠኝ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

መይ እሁድ 19 ቀን 2019 ዘጠኝ ስደተኞች በመያዝ በእንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ እንግሊዝ በመሄድ ላይ የነበረ ትንሽ ጀልባ...
ተጨማሪ ያንብቡ