ዋስትና ያለዉና ህጋዊ አማራጭ ለኢትዮጰያውያን

በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች ያለ ምንም ፍቃድና ቪዛ ወደ ሌላ ሃገር ለመሄድ (ለመሰደድ) ይሞክራሉ። አብዛኛዎቹ ህገወጥ ስደተኞችና ተጓዦች በየመንገዱ ለሚያጋጥማቸው ገንዘባዊ ፣ አካላዊና ስነ አእምሮራዊ ችግርና የሚያስከፍለውነ ዋጋ እውቀት የላቸውም። አንዳንዳቹ ጊዚያቸውና ገንዘባቸው ያጠፋሉ ፣ ሌሎች ደግሞ ችግር መከራ ብዝበዛና እንግልት ሌሎቹ ደግሞ ህይወታቸውን እሰከማጣት ይደርሳሉ።

አንተ ራስህ ወይም ሌላ የምታውቀው ሰው ኢትዮጵያን ለቆ ያለ ህጋዊ ቪዛ ወደ ሌላ ሃገር ለመስራትና ለመኖር ታስባለህ ? እንደዛ የምታስብ ከሆነ ይህንን መመሪያ አንብብና (በማንበብ) ዋስትና ያላቸው አማራጮች በህጋዊ መንገድ የመጓዝ ዘዴና በሃገርህ የስራ ውስጥ እድል ማግኘት ይቻላል።


አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች መንግስታት የአውሮፓ ህብረት ብሉ ካርድ (ሰሚያዊ ካርድ) የስራ ቪዛ ፕሮግራም (መርሃ ግብር) የተባለዉና ልዩ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ፕሮፌሽናሎች ከሌሎች አገሮች የሚስብ ዘዴ ይጠቀማሉ (ይሳተፋሉ)።

የአውሮፓ ህብረት ሰማያዊ ካርድ (ብሉ ካርድ) ኔትወርክ የተባለ ከፍተኛ ችሎታና እውቀት ያላቸው ሰራተኞች ከአውሮፓ ህብረት ውጭ የሆኑ ከአውሮፓያን አሰሪዎች ጋር የሚሰሩ ያገናኛል። የስራ እድል ካጋጠመህ ለአውሮፓ ህብረት ብሉ ካርድ ለመመዝገብ ማመልከት ይቻላል። ለመመዝገብ ብቁ ለመሆን የሚቻለው ባለህ የስራ እድል እና  የትምህርት ደረጃ ነው የሚወሰነው።

የአውሮፓ ህብረት ሰሚያዊ ካርድ ያላቸው የመግቢያና የመኖርያ ፈቃድ አስቀድሞ ይሰጣቸዋል። ይህ ማለት ደግሞ ወደ አውሮፓ ህብረት ህጋዊና ያለ ምንም ችግር ሊጓዙ ይችላሉ። አብዛኛው ጉዳይ ቤተሰቦቻቸው ሊያመጡና የቋሚ መኖርያ ፈቃድ ለማግኘት ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ሊያመለክቱ ይችላሉ።

በአውሮፓ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እድል ካገኘህና የትምህርት ክፍያ መክፈል የምትችል ከሆነ ለተማሪ ቪዛ መመዝገብ ትችላለህ። ትምህርትህ እንድትከታተል ያስችልሃል ፣ በአውሮፓም መዘዋወርና በትርፍ ጊዜህም ስራ መስራት ያስችልሃል።

የተጨማሪ ሸንገን ቪዛ ከአውሮፓ ህብረት አገራት ውጭ ለሆኑ ተማሪዎች በሸንገን ዞን ሃገሮች እስከ ሶስት ወራት ድረስ መቆየት ይፈቀድላቸዋል። በአውሮፓ ለረዥም ጊዜ ለመኖርና ለመማር ለረዥም ጊዜ ትምህርትና መቆየት ቪዛ በአገርህ ውስጥ በሚገኘው ባለው ኤምባሲ ማመልከት ይቻላል።

በአውሮፓ ዩኒቨርስቲዎች የትምህርት ክፍያ ውድ ቢሆንም ህገወጥ ስደት ደግሞ ከዛ የባሰ ነው የሚያስወጣው። አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ልዩ ችሎታ ላላቸው ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል (ስኮላርሽፕ) ይሰጣሉ።

እንደየሃገሮቹ ህጎች ሁኔታ በአውሮፓ መኖርና መማር ነዋሪነት ፈቃድ ለማግኘት እንደታመልክት ምቹ ሁኔታ ያመቻችልሃል።

በትህምህርት ጎበዝ ሆነህ የትምህርት ክፍያ መሸፈን የማትችል ከሆንክ ለነፃ የትምህርት እድል (ስኮላርሽፕ) መርሃ ግብር ማመልከት ይቻላል። ለምሳሌ በአውሮፓና በዓለም ዙርያ ለአፍሪቃ ብዙ ተማሪዎች የነፃ ትምህርት እድሎች አሉ። የእስላማዊ የልማት ባንክ ለጎበዝ ተማሪዎች በአባል ሃገራት ለስኮላርሽፕ ክፍያ ያደርጋል  አባል ባልሆኑት አገሮች የሙስሊም ማህበረሰብ ጭምር ይከፍላል።

ነፃ የትምህርት እድልን በተመለከተ ዩኒቨርሰቲው በሚገኝበት የአውሮፓ ህብረት አገር ለመኖር እንዲፈቀድልህ ለተማሪ ቪዛ ማመልከት ትችላለህ ፤ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ደግሞ ለሌላ ዓይነት የተለየ ቪዛ ወይም ለቋሚ መምርያነት ቪዛ ማመልከት ትችላለህ።

በአፍሪቃ ዩኒቨርስቲዎች ለመማርም የነፃ ትምህርት እድሎች አሉ። ለምሳሌ የምውአሊሙ ኔሬሬ የአፍሪቃ ህብረት የነፃ ትምህርት መርሃ ግብር ተገን ጠያቂ ስደተኞችና ከአፍሪቃ የተፈናቀሉ በታወቁ የአፍሪካ ዩኒቨርሰቲዎች እንዲማሩ የሚያስችል ትምህርት እድል ነው።

አንድ ስደተኛ የተገን ጠያቂነት እደል ካገኘ ወይም በአውሮፓ ሃገር ሕጋዊ  የመኖርያ ፈቃድ ካለው ባለቤቱ/ቷ ወላጅ ወይም ልጁ ሊወስድ ይችላል። ለቤተሰብ ቅልቅል ለማቀው እዚህ ተጫን።

ጥገኝነት መጠየቅ መሰረታዊ መብት ነው። ሰዎች በአገራቸው በእስር ፣ ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታዎች ሲያጋጥማቸውና እንግልት ሲበዛባቸው የዓለም አቀፍ ከለላ እንዲያገኙ መብት አላቸው። በአጠቃላይ የተ.መ.ድ አባል ሃገራትና የተ.መ.ድ የሰደተኞች ከፍተኛ ኮምሽን   በ1951 ዓ/ም እ.ኤ.አ የወጣውን የተገን (ጥገገኝነት) ጠያቂዎች ስምምነትን በመከተል ለተገን ጠያቂ ብቁ የሆነው ማነው ብለው ይወስናሉ። ይህም ሲባል በአብዛኛዎቹ የአለም ክፍሎች የተገን ጥያቄ በአንድ ዓይነት የህግ  ማእቀፍ ነው የሚዳኘው። የአውሮፓ ህብረት ሃገራትም ወጥ የሆነ የአውሮፓ የተገን (ጥገኝነት አቀባበል አሰራር ዘርግተዋል።

በተናጠልም እያንዳንዱ ሃገር የራሱ የሆነ ህግና የአሰራር ደንብ መመሪያ አለው። ይህ መመሪያ ባለስለጣናት የተገን ጠያቂዎች ጥያቄዎች እንዴት እንደሚጠሩ ዝርዝር መመሪያ ይሰጣቸዋል።

 

የጥገኝነት ጥያቄ በሌላ አገር ካቀረብክና የጠየቅከው አገር እዛው እንድትቆይ ፈቃድ ካልሰጠህ ወደ ሌላ  በሕጋዊና ሰለማዊ ሁኔታ የምትሰራበትና የትምኖርበት ሶስተኛ  አገር እንድትላክ እድል አለህ።

ወደ ሌላ አገር የማሸጋገር ስራ ማለት አንድ ጥገኝነት ጠያቂ ጥገኝበት የጠየቀው አገር እዛው ለመኖር ፈቃድ ሳይሰጠው ሲቀርና ለሌላ አገር ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ (ጥያቄው) ተቀባይነት ሲያገኝ ወደ ተቀባይ አገር መላክ ማለት ነው።  ለማቀው እዚህ

ምንም እንኳን አውሮፓ ለስደተኞች ተመራጭ መደረሻ ብትሆን ባለህበት አከባቢ በሌላ ክፍለ ዓለም የስራ እድል ማግኘትና የመኖርያ ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል።

ለምሳሌ በኡጋንዳ ጥገኝነት ጠያቂዎች የመንቀሳቀስ ነፃነት ፣ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ለህክምና እና ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። የመስራትና የግል ንግድ ስራም ሊያካሂዱ ይችላሉ።

ብዙ አፍሪቃውያን በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስና ባህረ ስላጤ የስራ ቪዛ ይሰጣቸዋል ፤ እዛም በህጋዊና ሰለማዊ መንገድ ኑሮአቸውን ይመራሉ።

መንግስታት ፣ የግል በለሃብቶችና ሌሎች ድርጅቶች ብዙ ሰዎች የሚሰደድባቸው ሃገራት ላይ  መዋእለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ናቸው። ይህም በውጭ አገር ገንዘብ ለማጣራቀምና የተሻለ ኑሮ ለመኖር ሲባልየወጣቶችን  ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ነው። ይህንን ዝርዝር የሚያሞላክተው ነገር ቢኖር በአገር ውስጥ ህይወትህን የሚቀይርና የተሻለ የኑሮ ሁኔታ የሚፈጥር በአገር ውስጥ መኖሩ ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ የስደተኞችን ኑሮ ቀዋሚ ፣ የተረጋጋና ጥሩ ህይወት እንዲኖራቸው የሚያስችል ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ተቀርፀዋል። ለዚህም ሲባል  በአለም ባንክና በአውሮፓ ህብረት የተዘጋጀ አዲሰ የስራ ፈጠራ ፓኬጅ ለ30 ሺህ  አዳዲስ  ለስደተኞችና ተገን ጠያቂዎች የሰራ እድል የሚፈጥር ተዘጋጅቷል።

የቴክኒክና የሞያ ስለጠናዎችም ኢትየጵያ ውስጥ ባሉ የእድርታ ድርጅቶች በተለይም ለስደተኞች (በስደተኞች ማእከላት በከተማ ማእከላት) እየተሰጠ ነው። ለምሳሌ በኖርወይ የስደተኞች ካውንስልና በጀስዊት የሰደተኞች አገልግሎት የተባሉ ድርጅቶች በቧንቧ ስራ ፣ ኤሌክተሪክ ጥገና ፣ ብረታ ብረትና የእንጨት ስራዎች ስለጠናዎች እየተሰጡ ናቸው።

በኖርዋይ ስደተኞች ካውንስል በኢትዮጵያ ለንግድ ስራ መጀመር የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል።  በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ለሰለጠኑ ስደተኞችና መጠለያ ውስጥ ላሉ ሁሉ ስለጠና ይሰጣል።

ብዙ የአለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖችና ድርጅቶች እንደ ማይክሮሶፍትና ሲመንስ ያሉት የሞያ ስለጠናዎች ለአፍሪቃ ወጣቶች ይሰጣሉ። ልማት, ፋይናንስና ቴክኖሎጂን ጨምሮ በዚህ ሰፊ ዘርፎች የሥራ ልምድ ለማግኘት እድሎችን ያግኙ።

በአብዛኛዎቹ አገሮች የቴክኒክ ሞያ ስለጠናዎች በእርሻ ገበሬዎች ገቢያቸውን እንዲጨምር በአፍሪቃ ልማት ባንክ በኩል የተዘጋጀ ውድድር አለ። ይህም የፈጠራ ስራ በመጠቀም ምርታማንነትና የእርሻ ቢዝነስ የሚያበረታታ ሽልማት ይሰጣል። ውድድሩ ለማንኛውም በአፍሪቃ የሚኖርና እድሜው ከ18 እሰከ 35 ዓመት ለሆነ ክፍት ነው።

ዋስተና ለሌለውና ህገወጥ ለሆነ የሰደት ጉዞ ገንዘብን ከማባከን ይልቅ በአከባቢህ ገንዘብ አጠራቅመህ ሰራ ብትጀምር ይሻላል።  በአካባቢህ ከሚገኙ አንሰተኛ የብድርና የገንዘብ ተቋማትና የእርዳታ ድርጅቶች በማመልከት  ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በማግኘት የንግድ ስራ  መጀመር ይቻላል።

በዚህ በዲጅታል ኢኮኖሚ እጅግ በጣም ብዙ እድሎች ሞልቷል። ስለ ኮዲንግ እና ፕሮግራሚንግ ኮርሶች ራስህ በኦንላይን /ቀጥታ መስመር በመግባት / በነፃ መማር ይቻላል። እንደ ሙክ እና ኦፕን ክላስ ሩም ገብተህ።  ዩዝ ኮኔክተ የተባለው ለአፍሪቃ ወጣቶች ጥሩ የስራ ፈጠራ ሰዎች እንዲሆኑ እድል ያመቻቻል፡ በቴክኖሎጅው ኢንዱስትሪም እንዲሰሩ ያግዛል።

ለሌላ ያካፍሉ

የእንገሊዝ ቻናል በማቋረጥ ላይ ለነበሩ ስደተኞች ድጋፍ አድርጋቹኋል የተባሉ ሁለት ፈረንሳውያን ታሰሩ

ሁለት ፈረንሳውያን ስደተኞች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው ወደ እንግሊዘ እንዲገቡ በማገዛቸው ምክንያት በእስር እንዲቀጡ...
ተጨማሪ ያንብቡ

በፓሪስ አየር መንገድ ተርሚናል በሀይል ወደ ሀገር ቤት አንመልስም ያሉ በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሰለማዊ ሰልፍ አደረጉ

በመተዎች የሚቆጠሩ ህገ ወጥ ስደተኞች በፈረንሳይ መዲናዋ ፓሪስ ከተማ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ በመሰባሰብ...
ተጨማሪ ያንብቡ

የፈረንሳይ የባህር ላይ ጥበቃ ሀይሎች የእንግሊዝ ቻናል አልፈው ለመሄድ የሞከሩ ዘጠኝ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

መይ እሁድ 19 ቀን 2019 ዘጠኝ ስደተኞች በመያዝ በእንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ እንግሊዝ በመሄድ ላይ የነበረ ትንሽ ጀልባ...
ተጨማሪ ያንብቡ

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ